Page 71 - አብን
P. 71

አብን


             እንዳለባቸው  ይታመናል፡፡  ነገር  ግን  የፍልስፍና  መሰረት

             የሌላቸውን  የማደራጃ  መርሆዎች  የፖለቲካ  ስልጣን  ምንጭ
             ማድረግ  ያጋጠመንን  ችግርና  ስጋት  የሚያራዝም  ከመሆኑም
             በላይ  በራሱ  ዘላቂ  ችግር  የሚፈጥር  መሆኑን  መዘንጋት
             አይገባም፡፡ የብሄር ማንነትን የፖለቲካ ስልጣን መሰረት ያደረገ
             ስርዓት      የመንግስትና         የሀይማኖት          መለያየትን        ጉዳይ
             በመርህነት  መከተል  አይችልም፡፡  ሀይማኖትን  ከመንግስት
             መለየት  ያስፈለገበት  ታሪካዊና  ነባራዊ  እንዲሁም  የመርህ
             ምክንያቶች  የብሄረሰብ  ማንነትን  ከመንግስት  ለመለየት  በቂ

             ምክንያቶች ናቸው፡፡ በሀገራችን ውስጥ እስካሁን ያለው መርህ
             አልባ የፖለቲካ ስርዓት በጽንሰሀሳብ ደረጃ                   የብሄር ማንነትን
             የፖለቲካ  ስልጣን  መሰረት  ያደረገ  ሲሆን  የበርካታ  ዜጎችን
             የፖለቲካ  ውክልና  እንዲሁም  አጠቃላይ መሰረታዊ  መብቶችን
             የነፈገ  ነው፡፡  በተግባርም  የጭቆናና  የቅራኔ  ማዕቀፍ  ሆኖ
             ይገኛል፡፡  መንግስታዊ  ስልጣን  አብዛኛውን  ህዝብ  ለመበደልና

             ለማግለል  ስራ  ላይ  ስለሚውል  የአናሳ  አምባገነኖች  ስርዓት
             እውን ይሆናል፡፡ በዚህም በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ የስልጣን
             ሽግግር  ምትክ  “በኛና  በነሱ”  ቅኝት  ቅርቃር  ውስጥ  ባለ
             የማህበረ  ፖለቲካ  ውስጥ  የጎለበቱ  ልሂቃን  ጥላቻን  እየሰበኩ፤
             ቅራኔን እያነገሱና ህዝቡን እየከፋፈሉ የሴራና የሙስና  ባህል
             ገንብተው        የደምበኝነት        ፖለቲካ       /clientilism/   ባለበት
             እንዲቀጥል  ያደርጋሉ፡፡  የዚህ  አይነት  መንግስታዊ  ብሂል
             ህዝብን ላልተቋረጠ ግጭት እንዲሁም ሀገርን ለመፍረስ አደጋ

             የሚዳርግ ይሆናል፡፡

             አብን  ለበርካታ  መሰረታዊ  መብቶቻችን  አለመከበርና  መጣስ
             እንዲሁም  በሀገራችን  አንድነት  ላይ  መናጋት  የሚፈጥረው

               69   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   66   67   68   69   70   71   72   73   74   75   76