Page 26 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 26
አብን
የህውሓትን የኢኮኖሚ ልማት ሞዴል እየተከተሉ ማለትም
አልሚውን ሳይሆን የዘውግ ተመሳሳይነት መመዘኛን
የሚያሟሉ የኢኮኖሚ ተዋንያኖችን ብቻ እያበለፀጉ ዘላቂነት
ሊኖረው የሚችል የኢኮኖሚ ልማት ለማስገኘት አይቻልም፡፡
1.8. የኦሮሞ ብልጽግና አዲስ አበባን በተመለከተ
የሚከተለው የተረኝነት ፖለቲካ
ትክክለኛው ታሪክ በተገቢ መረጃ አስደግፎ የሚያስረዳን በራራ
ወይም ቀዳሚት አዲስ አበባ በግራኝ አህመድ ጦር በ1531
ዓ.ም ተቃጥላ እንድትወድም ከተደረገ በኋላ፣ የአጼው ንጉሠ
ነገስታዊ እና የግራኝ ጦር የፍልሚያና የዘመቻ ስምሪት
ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማለትም ከሸዋ ወደ ሰሜን እየተገፋ
መሄዱን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታውን ያስለቀቁት የቱለማ
ኦሮሞ ጎሳዎች እነሱ ሸዋ ከመድረሳቸው በፊት በቦታው የነበሩ
በአብዛኛው የአማራ፣ በከፊል የጉራጌ የጋፋት፣ የአርጎባ የማያ
እና ሌሎች ማህበረሰቦችን በሃይል አስወግደውና አፈናቀለው
በቦታው ላይ በቋሚነት ሊሰፍሩ መቻላቸውን ነው፡፡ በመሰረቱ
የኦሮሞ ነገዶች ወደ ኢትዮጵያ ደጋ መሬቶች መግባት
የጀመሩት ነጮች ማለትም እንግሊዞች እና ደቾች ደቡብ
አፍሪካን በቅኝ ግዛትነት ከያዙበት ዘመን ጋር የሚገጣጠም
ነው፡፡ ነጮች ደቡብ አፍሪካን በወታደራዊ ሃይል ተቆጣጥረው
የአፓርታይድ አገዛዝ ለዘመናት ለማስፈን ቢችሉም፣ በቦታው
ቀዳሚ ነዋሪ የሆነውን ጥቁር ህዝብ የእኩል የፖለቲካ
ተሳታፊነት እና የአገር ባለቤትነት መብቱን እስከ መጨረሻው
አግደው ሊይዙ አልቻሉም፡፡ የደቡብ አፍሪካ ፖለቲካ ከዘር
ፖለቲካ ተላቆ ወደ ዲሞክራሲ ስርዓት ለመሸጋጋር የቻለው፣
24 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !