Page 30 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 30
አብን
ስትራቲጂያዊ /የረዥም እይታ/ እና መዋቅራዊ ስጋቶች
1.9.1. ውስጣዊ ስጋቶች
ሀ/ ኢኮኖሚያዊ
የሃገሪቱ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ
በመምጣቱ እና ካለፉት ዓመታት የቀጠሉ መዋቅራዊ
ችግሮች እንደተጠበቁ ሆኖ ባለፉት ሶስት ዓመታት
የኢኮኖሚው እድገት በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት
የተገታ በመሆኑ የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ
እያሽቆለቆለ መምጣቱ፤
በአፈር መከላት በዛፎችና በእፅዋት መመናመን፣
በበርሃማነት መስፋፋት ምክንያት የሃገሪቱ ስነ ምህዳር
እየተመናመነ መሄድ፤
የግብርናው ዘርፍ ሥር የሰደደ መዋቅራዊ ችግር፣
ቋሚ እየሆነ የመጣ የምግብ እጥረት፣ በየጊዜው
የሚከሰተው ድርቅ አንድ ላይ ሁነው የህዝቡን ኑሮ
ከፍተኛ ችግር ላይ መጣላቸው፤
በገጠር እና በከተማዎች ድህነት መባባስ ሳቢያ የወጣት
ሥራ አጦች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሄዱ፣
የዘውግ ብሄርተኝነትን መሰረት አድርጎ በሃገሪቱ ውስጥ
የሚካሄደው መረን የለቀቀ ሙሰኝነት ከዚህም ጋር
ተያይዞ ከገዥው የዘውግ ልሂቃን ጋር በመሞዳሞድ
የፖለቲካ ትስስሩን ወደ ሃብት የሚለውጥ ተጠዋሪ
ባለሃብት /Patronage/ የሚያጋብሰው ከሥራ ውጤት
ጋር ያልተያያዘ ጣራ በነካ ገቢ ምክንያት የሃገሪቱ
የሃብት ክፍፍል በከፍተኛ ደረጃ መዛባቱ፣
28 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !