Page 34 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 34

አብን


             ከዚህ በተጨማሪ የቆየው የሱማሌ ብሔርተኝነት እና በምስራቅ

             አፍሪካ  ያሉ  የሱማሌ  ህዝብ  የሰፈረባቸውን  ልዩ  ልዩ  ግዛቶች
             ወደ አንድ ለማሰባሰብ ያለ ህልመኝነት ጨርሶ ሊጠፋ ያልቻለ
             የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የስጋት ምንጭ ነው፡፡

             ለ/ ደቡብ ሱዳን


             በደቡብ  ሱዳን  ውስጥ  ባሉ  ዋና  ዋና  ጎሳዎች  መካከል  (ዲንካ
             እና  ኑዌር)  ከነፃነቷ  በኋላ  የተቀጣጠለው  የእርስ  በርስ
             ጦርነት፣  በጦርነቱ  ሳቢያ  ወደ  ኢትዪጵያ  የሚፈልሱ  የደቡብ
             ሱዳን  ዜጎች  መበራከት  በኢትዮጵያ  ላይ  የኢኮኖሚ  እና
             የደህንነት  ስጋት  ፈጥሯል፡፡  በተለይም  ደግሞ  ወደ  ኢትዮጵያ
             የሚፈልሱ  በአብዛኛው  የኑዌር  ጎሳ  አባላት  መሆናቸው  እና
             ከእነዚህ  ውስጥ  ደግሞ  ወደ  450,000  የሚጠጉ  በጋምቤላ

             የሰፈሩ  የደቡብ  ሱዳን  ኑዌሮች  በኢትዮጵያ  መንግስት  ፈቃድ
             ኢትዮጵያዊ  ዜግነት  እንዲፈቀድላቸው  መደረጉ  ወደፊት
             የጋምቤላን  ክልል  ብሄረሰባዊ  ጥንቅር  በመቀየር  ለኢትዮጵያ
             ሃገራዊ ደህንነት የስጋት ምንጭ መሆኑ የማይቀይር ነው፡፡

             ሐ. ሱዳን


             በረዥም  ጊዜ  የጉርብትና  ታሪካቸው  ሱዳን  እና  ኢትዮጵያ
             ወዳጅነት የፈጠሩበት ጊዜ በወያኔ ዘመን ነው ቢባል ከእውነቱ
             መራቅ  አይሆንም፡፡  ሱዳን  የፖለቲካ  እስልምናን  በፖሊሲነት
             መከተል  የምትታወቅ  መሆኗ  ይህ  ፖሊሲዋ  የሚያቀራርባት
             ከግብፅ እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር ሊሆን አይችልም፡፡






               32   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   29   30   31   32   33   34   35   36   37   38   39