Page 36 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 36

አብን


             ጅቡቲም  ከዚህ  አንፃር  የስጋት  ምንጭ  ልትሆን  አትችልም

             ብሎ  መደምደም  አይቻልም፡፡  በተለይም  ወደ  ኢትዮጵያ
             የሚገባን የጦር መሳሪያ በማገድ ረገድ ኢትዮጵያን ለማጥቃት
             ለሚፈልግ  ሃገር  ተባባሪ  የምትሆንበት  ሁኔታ  ቢፈጠር፣
             በሃገራችን ላይ አደገኛ ሁኔታ እንደሚፈጠር መገመት ይቻላል፡

             ሠ. ኤርትራ

             የኢትዮጵያ  እና  ኤርትራ  ግንኙነት  የመሪዎች  ግንኙነት
             ከመሆን  አልፎ  የሁለቱን  ሀገሮች  ህዝብ  ታሪካዊ  ትስስር
             በሚመጥን  መልኩ  ግልፅ  እና  ይፋ  የሆነ  ስምምነት  ላይ
             ሊደረስ  ይገባል  ብለን  እናምናለን፡፡  ህወሓት  ለሃገር  ሳይሆን
             ከድርጅት  ጥቅሙ  አንጻር  ብቻ  በመነሳት  በኢትዮጵያ  ውስጥ
             ተገዳዳሪ  ሃይል  እንዲኖር  ባለመፈለጉ፣  ቀዳሚ  እውቅና
             በመስጠት ለኤርትራ መገንጠል ሁኔታዎች አመቻቸ፡፡ ኤርትራ
             እራሷን  የቻለች  ሀገር  ከሆነች  በኋላ  ግንኙነቱን  ሃገራዊ

             ግንኙነት  ከማድረግ  ይልቅ  በድርጅታዊ  ግንኙነት  ስለወሰነው፣
             ይህ  መርህ  አልባ  ግንኙነት  ቆይቶ  ወደ  አስከፊ  ጦርነት
             ሊያመራ ችሏል፡፡ ከጦርነቱ በኋላ ከሁለቱ ሃገሮች ዘላቂ ጥቅም
             አንፃር ግንኙነቱን ማሻሻል ሲገባ፣ ህወሓት ኤርትራን በዓለም
             ማህበረሰብ  እንድትገለል፣  በኢኮኖሚ  ጫና  እንድትንበረከክ
             ማድረግን አልሞ ሰርቷል፡፡


             ከዘለቄታዊ ጥቅም አንፃር የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝብ በዚህ
             ሁኔታ ተነጣጥሎ መኖር መቀጠሉ ለሁሉም ቢሆን የሚጠቅም
             አልነበረም፡፡  እንዳልሆነም  ያለፉት  ሰላሳ  ዓመታት  ልምድ
             በተጨባጭ አረጋግጧል፡፡




               34   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   31   32   33   34   35   36   37   38   39   40   41