Page 41 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 41

አብን


             ፋይናንስ  ዘርፉ  ካሉ  አገልግሎቶች  ይልቅ  በተለመዱት

             የሆቴልና  መስተንግዶ  ዘርፎች  ያተኮሩ  ቢሆንም  ዕድገቱ
             ከፍተኛ ሊባል የሚችል ነው። በተመሳሳይ ጊዜ የኢንዱስትሪው
             ድርሻም  ከነበረበት  13  በመቶ  ወደ  26  በመቶ  አድጓል፡፡
             የኢንዱስትሪ  ዘርፉ  ለኢኮኖሚው  ያለው  አስተዋጽኦ  በከፍተኛ
             ሁኔታ  ያደገ  ቢሆንም  የዘርፉ  ዋነኛው  ኢኮኖሚ  እንቅስቃሴም
             በአመዛኙ  የግንባታ  ዘርፉ  ላይ  የተንጠለጠለ  ሲሆን  የአምራች
             ዘርፉ አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን እስከአሁንም
             ድረስ  ግብርናው  ለአገራችን  ማህበራዊና  ኢኮኖሚያዊ  ዕድገት

             እያደረገው  ያለው  አስተዋጽኦ               የጎላ  ነው፡፡  ምንም  እንኳ
             ለተከታታይ  ዓመታት  ከፍተኛ  ሊባል  የሚችል  ዕድገት
             ቢመዘገብም  የ2011ዓ.ም  ጥቅል  አገራዊ  ምርትን                     (GDP)
             ለአብነት ብንወስድ 84.3 ቢሊየን ዶላር ወይም 2.2 ትሪሊየን
             ብር  ብቻ  ነው፡፡  ይህ  አገራዊ  ምርት  ለ100  ሚሊየን  ህዝብ
             ሲከፋፈል በዓመት በነፍስ ወከፍ 843 ዶላር ወይም 22 ሺህ

             ብር ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡

             ምንም  እንኳን  በአሀዝ  ደረጃ  ዕድገት  የተመዘገበ  ቢሆንም
             በግልጽ  የተስተዋሉ  የኢኮኖሚ  ተግዳሮቶች  ነበሩ፡፡  ከነዚህም
             መካከል፡-

                   እየሰፋ የመጣ የገቢ አለመመጣጠን፣
                   የነጋዴውንና ኢንቨስተሩን የፋይናንስ እጥረት መቅረፍ
                     ያልቻለ፣  ደካማና  ያልዳበረ  የፋይናንስ  ተቋማትና
                     ገበያ፤

                   ዝቅተኛ ምርታማነት (ግብርናን ኢንደስትሪ)፣




               39   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   36   37   38   39   40   41   42   43   44   45   46