Page 44 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 44
አብን
፡ ይህም ሃገሪቱ ለሚደርስባት ያልተገባ የውጭ ጣልቃ
ገብነት እና ተፅዕኖ ከፍተኛ በር ይከፍታል፡፡
በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ የመጣ የወጣቶች ስራ
አጥነት በተለይ በከተሞች አካባቢ ችግሩ በከፍተኛ
ሁኔታ ስር የሰደደ ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ብቻም ሳይሆን ስር
የሰደደ የችሎታና የመፈጸም ችግር አለበት፡፡ ለልማት
ፓሊሲዎችና ለኢኮኖሚ ዕድገቱ አስተዋጽኦ ሊያበርክት
የሚችል ከፍተኛ የሆነ የክህሎትና የዕውቀት ክፍተትም
ይስተዋላል፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ሃገሪቱ ያላት
የሰው ሃይል የምርታማነት መለኪያ በዝቅተኛ
የኢኮኖሚ ዕደገት ደረጃ ካሉ ሃገሮችም በንፅፅር ያነሰ
መሆኑ ነው፡፡ እንደ አለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት
መረጃ በ 2010 ዓ.ም አጠቃላይ አመታዊ ምርት
በአምራች ሃይል ከ4000 ዶላር በታች ነው፡፡ በዝቅተኛ
ኢኮኖሚ ዕድገት ደረጃ ያሉት አገሮች አማካይ
ምርታማነት ደግሞ 5000 ዶላር ነው፡፡
ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገቱ መቀዛቀዝ፡- እንደ
አለምአቀፉ ገንዘብ ድርጅት /IMF/ መረጃ ከሆነ
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት በ 2011 ዓ.ም ከነበረው
8.97 በመቶ ምጣኔ በ 2012 ዓ.ም ወደ 1.95 በመቶኛ
የወረደ ሲሆን በያዝነው የበጀት አመት መጨረሻም 0
በመቶ እንደሚሆን ተተንብይዋል፡፡
በየአመቱ እየጨመረ የመጣ የዋጋ ንረት ችግር፡- እንደ
IMF መረጃ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ከነበረበት 6.6
በመቶኛ ምጣኔ እያደገ መጥቶ በ2012 ዓ.ም መጨረሻ
42 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !