Page 40 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 40
አብን
2. የኢኮኖሚ ችግሮች
2.1 ጠቅላላ
የኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የኢኮኖሚ ዕድገት በዋነኝነት
የመንግስት መር ኢኮኖሚና የልማት መር ፓሊሲ ውጤት
ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይህ ዕድገት በአመዛኙ የተመዘገበው
መንግስት በስፋትና በፍጥነት በተሰማራባቸው የመሰረተ
ልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ላይ በተደረገ ኢንቨስትመንት
ነው፡፡ ባለፈው አስር አመት ለሚጠጋ ጊዜ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
የማገገምና ዕድገት የማስመዝገብ አዝማሚያ በማሳየት በዓመት
በአማካይ 10.4 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል (የዕድገት
ምጣኔው ከፍ እንዲል ያደረገው ከዝቅተኛ መሰረት /low
base/ መነሳቱና ምቹ ውጫዊ ሁኔታዎች መኖራቸውን ግምት
ውስጥ መግባት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት
ነው)፡፡ በተለይ በቂ ዝናብ በተመዘገበባቸው ዓመታት የግብርና
ምርታማነት ዕድገት ተመዝግቧል፡፡ የካፒታል ክምችትም
መጠኑም (ጥቅል የሃብት ፈጠራ/gross capital formation/፣
ጥቅል የአገር ውስጥ ቁጠባ /gross domestic savings/፣
የሃብት መጠን /resource balance/፣ የተጣራ ወቅታዊ
ሽግግር /net current transfer/ ከአገራዊ ምርት ዕድገቱ ጋር
በንጽጽር በመቶኛ (as percent of GDP) ሲታይ ዕድገት
አስመዝግቧል፡፡
የኢኮኖሚ መዋቅሩም የግብርና ዘርፉ አስተዋጽኦ ከ52 በመቶ
ወደ 36 በመቶ ሲቀንስ በአንጻሩ የአገልግሎት ዘርፉ በ1997
ዓ.ም ከነበረበት 13 በመቶ ወደ 38 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡
፡ ምንም እንኳን የአገልግሎት ዘርፉ ዕድገት እንደ አይሲቲና
38 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !