Page 42 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 42

አብን


                   ማሽነሪዎችን           ጨምሮ         የካፒታል         ዕቃዎችንና

                     ቴክኖሎጂን  ከውጭ  ለማስገባት  ከፍተኛ  የውጭ
                     ምንዛሬ እጥረት መኖር፤
                   የውጭ  ዘርፉ  ዕድገት  አዝጋሚ  በመሆኑ  አገራችን
                     ከፍተኛ  የውጭ  ዕዳ  ጫና  ካለባቸው  አገራት  ተርታ
                     እንድትሰለፍ  አድርጓታል፡፡  ይህን  ችግር  ለመቅረፍና
                     የውጭ  ምንዛሬ  እጥረት  ለመቅረፍ  የብር  የመግዛት
                     አቅም  እንዲቀንስ  የማድረግና  የመንግስት  ድርጅቶችን
                     ወደ ግሉ ዘርፍ የማዞር ስራ እየተሰራ ነው፡፡

                   ስር የሰደደ ድህነት አሁንም የአገራችን ከፍተኛ ችግር
                     ነው፡፡ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ልማት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ
                     ደረጃ  ያለት  ሲሆን  ከ189  አገሮች  173ኛ  ደረጃን
                     እንደያዘች ናት (የተ.መ.ድ የልማት ፕሮግራም/2018)፡
                     ፡  10  በመቶ  የሚሆነው  ህዝቧ  አሁንም  ድረስ
                     በከፍተኛ  የምግብ  ዋስትና  ችግር  ውስጥ  ያለ  ሲሆን

                     ሰፊ  ቁጥር  ያለው  ህዝቧም  ከእጅ  ወደ  አፍ  በሆነ
                     ግብርና ላይ ጥገኛ ነው፡፡
                   ሌላው  ተግዳሮት  የኢኮኖሚ  ዕድገቱን  ሊያስቀጥል
                     የሚችል  በቂ  መዋቅራዊ  ማሻሻያ  ማድረግ  ባለመቻሉ
                     ባለፉት  3  ዓመታት  የኢኮኖሚ  ዕድገት  መጠኑ                   ከ8
                     በመቶ  በታች  ዝቅ  ብሏል፡፡  የኢትዮጵያ  ኢኮኖሚ
                     ዕድገት  በሶስት  ደረጃዎች  የመዋቅራዊ  ክፍተት
                     አሳይቷል፡-

                            ምንም  እንኳ  ከፍተኛ  የፓለቲካ  ድጋፍና
                             የበጀት  ምደባ  ቢደረግለትም  የኢትዮጵያ




               40   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   37   38   39   40   41   42   43   44   45   46   47