Page 47 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 47

አብን


             ተዳምሮ  የግብርናው  ምርታማነት  እየቀነሰ  ከመሄድ  ሊገታ

             አልቻለም፡፡  ገዥ  ፓርቲው  በሚከተለው  የዘውግ  ፖለቲካ
             ምክንያት  በሕገ  መንግስቱም  በግልጽ  እንደተመለከተው
             በኢትዮጵያ ውስጥ መሬት በሃብት ማፍሪያነት የተያዘው በግል
             አምራች  ገበሬዎች  ሳይሆን፣  በብሔር  ብሔረሰቦች  ስለሆነ
             በሃገራችን  ተጨባጭ  ሁኔታ  መሬት  በፌደራል  እና  በክልል
             መንግስታት ባለቤትነት ስር ነው፡፡ በሥራ ላይ ያለው የመሬት
             ስሪት በሕገ  መንግስቱ መሰረት ገበሬውን  ከመሬት  ባለቤትነት
             ያገለለ  ነው፡፡  በመሬት  ላይ  የማዘዝ  ስልጣን  የሰጠው

             በመንግስት  ይዞታ  ስም  ለገዥው  ፓርቲ  የወረዳ  ካድሬዎች
             ነው፡፡

             ልክ  በህወሓት  ጊዜ  ሲደረግ  እንደነበረው  በብልጽግናም
             እየተተገበሩ  ያሉ  የግብርና  ፖሊሲዎች  ባለድርሻ  አካላትን
             አላሳተፈም፡፡  አራሹን  ገበሬ  በቴክኖሎጅ  አጠቃቀምና  በዘላቂ

             ኢንቨስትመንት          ውሳኔ       እንዳይሳተፍ        ማነቆ       ሆነዋል፡፡
             በግብርናውም  ሆነ  በሌሎች  የኢኮኖሚ  ዘርፎች  የግሉ  ክፍለ
             ኢኮኖሚ ተሳትፎ ወሳኝ ሆኖ እያለ፣ ህወሓትም ሆነ ብልጽግና
             በሚከተሉት  ተመሳሳይ  ርዕዮተአለም  ምክንያት  ከፕሮፓጋንዳ
             በዘለለ     የግሉ      ዘርፍ      በግብርናው        መስክ      እንዲሰማራ
             የተመቻቸለት  የፖሊሲም  ሆነ  የአፈፃፀም  ምህዳር  የለም፡፡
             ይህም  የግብርናው  ዘርፍ  ከቴክኖሎጅ  ሽግግር  ማለትም

             በዝቅተኛ  የግብዓት  አጠቃቀም፣  በመስኖ  ስራ፣  በግብርና
             ሜካናይዜሽን  እንዳይጠቀም  አድርጎታል፡፡  የግብርናው  ዘርፍ
             ለሀገሪቱ  ኢኮኖሚ  ያለውን  አስተዋፅኦ  ግምት  ውስጥ  ያስገባ
             የኢንቨስትመንት አቅርቦት የለም፡፡ የግብርናው ዘርፍ ተቋማዊ
             ችግር  የግብርና  እውቀት  ባላቸው  ባለሙያዎች  ሳይሆን

               45   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   42   43   44   45   46   47   48   49   50   51   52