Page 48 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 48

አብን


             በፖለቲካ  ካድሬዎች  ተፅዕኖ  ስር  የወደቀ  በመሆኑ  ዘርፉ

             ስትራቴጂያዊ  እይታ  የሚጎለው  በዘመቻ  ስራዎች  የታጠረ
             እንዲሆን አድርጎታል፡፡

             2.3.   የአካባቢ መጎዳት

             በኢትዮጵያ  በተደጋጋሚ  የሚከሰተው  ረሃብ  ዋነኛ  መንስኤ
             የአካባቢ  ስነ  ምህዳር  መጎዳት  ጋር  በቅርብ  የተጎዳኘ  ነው፡፡
             ከመሬት  ይዞታው  ስሪት  ጋር  በተያያዘ  ተገቢ  ባልሆነ  ሁኔታ

             እየተካሄደ  ያለው  የመሬት፣  የአፈር  እና  የውሃ  ሃብታችን
             አጠቃቀም ፣ እንዲሁም የደን መመንጠር ከባድ የአካባቢ ጉዳት
             አስከትሏል፡፡ ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት
             በመሬቱ  መጎዳት  ምክንያት  ሃገሪቱ  ትልቅ  አደጋ  ላይ
             መውደቋን  ያመለክታሉ፡፡  የገጠሩ  ሕዝብ  ቁጥር  ከሚገባው
             በላይ  እየጨመረ  በመሄዱ  እና  ከመሬት  ፖሊሲው  ጋር
             በተያያዘ  የመሬት  ጥበት  በመፈጠሩ  የሃገሪቱን  መሬት

             በይበልጥ  እንዲጎዳ  እያደረገው  ነው፡፡  ገዥው  ፓርቲ
             የሚከተለው  የመሬት  ሃብት  አጠቃቀም  ለሃገሪቱ  ኢኮኖሚ
             ያለውን  አስተዋፅኦ  ያልተገነዘበ  ፖሊሲ  በመሆኑ                   ለአካባቢው
             መጎዳት ከፍተኛ አስተዋፅኣ እያበረከተ ነው፡፡


             2.4.    የሃገራችን ገበያ በውጭ ሸቀጦች መወረር
             የሃገራችን  ገበያ  በውጭ  ሸቀጦች  መጥለቅለቁ  ለመካከለኛና

             አነስተኛ  ኢንዱስትሪ  እድገት  የተመቻቸ  ሁኔታ  እንዳይኖር
             አድርጎታል፡፡ በሃገራችን አነስተኛ ኢንዱስትሪ የሚባሉት ከ1.5
             ሚሊዮን  ብር  በታች  በስራ  ላይ  የዋሉትን  ሲሆን፣  መካከለኛ
             የሚባሉት  ደግሞ  ከ1.5.  እስከ  20  ሚሊዮን  ብር  በስራ  ላይ


               46   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   43   44   45   46   47   48   49   50   51   52   53