Page 49 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 49

አብን


             የዋሉትን  ነው፡፡  ከህወሓት  ጊዜ  ጀምሮ  አሁንም  በብልጽግና

             ፓርቲ  ዘመን  በቀጠለው  የቋንቋ  ፌደራሊዝም  አማካይነት
             የኢንዱስትሪው ዘርፍ በሚደርስበት የፖለቲካ እና መንግስታዊ
             ጫና  ምክንያት፣  የግሉ  ዘርፍ  አቅሙን  ሊያጎለብትና  በሃገሪቱ
             በፈለገው  ቦታ  ተዘዋውሮ  ሊሰራ  አልቻለም፡፡  ከ2012  ዓ.ም
             ጀምሮ  በተለይ  በኦሮሚያ  አካባቢ  ማንነትን  መሰረት  ያደረገው
             እልቂት እና የንብረት ውድመት የተነሳ፣ በየቦታው የወደሙት
             ኢንዱስትሪ  እና  የአገልግሎት  ተቋማት  ሃገሪቱን  ለማዘመን
             የሚችለው  የግል  ዘርፍ  ባለው  ሰፊ  እድል  እንዳይጠቀም

             አድርጎታል፡፡

             የአነስተኛ  እና  የመካከለኛ  ኢንዱስትሪው  ዘርፍ  እንዳያድግ
             በመስሪያ  ገንዘብ  እጥረት፣  ከውጭ  አለገደብ  በሚገቡ  ሸቀጦች
             ውድድር፣ በመስሪያ ቦታ ችግር፣ በሃይል እና ውሃ አቅርቦት
             ችግር፣  በመንግስት  ከሙሰኝነት  የፀዳ  አስተዳደር  ባለመኖሩ

             በሁለገብ ችግሮች ተተብትቦ ተይዟል፡፡

             2.5.   ያልለማ የማዕድን ዘርፍ

               የሃገሪቱ  የማዕድን  ዘርፍ  አለመልማት  ሌላው  የሃገራችን
               ኢኮኖሚ አይነተኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሃገራችን በማዕድን
               ሃብት  የበለፀገች  እንደሆነች  መረጃዎች  ቢጠቁሙም  በዚህ

               ዘርፍ የግሉ ባለሀብት እንዲሰማራ የተመቻቸ ሁኔታ የለም፡፡
               ህወሓትም         ሆነ     ብልጽግና        ወደ      ዘርፉ      እንዲገቡ
               የሚፈቅድላቸው  የግል  ኢንቨስተሮች  ከገዥው  ፓርቲ  ጋር
               ንክኪ  ያላቸውን  ብቻ  እንደሆነ  ይታወቃል፡፡  ዘርፉ  በባህሪው
               ከፍተኛ  ፋይናንስ፣  ዘመናዊ  ቴክኖሎጂ  እንዲሁም  የዳበረ
               ጥናትና       ምርምር        የሚጠይቅ         አንደመሆኑ         የውጭ

               47   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   44   45   46   47   48   49   50   51   52   53   54