Page 50 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 50
አብን
ኢንቨስትመንት ሊሳብበት የሚችል ዘርፍ ነው፡፡ ይሁንና
ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ የውጭ
አልሚዎችን በስፋት ለመሳብ አልተቻለም፡፡
2.6. የሃገሪቱ የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ ያለመሆን
በአንድ ሀገር ውስጥ ቀጣይነት ያለውና በፅኑ መሰረት ላይ
የቆመ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ለማምጣት ጠንካራና
የተረጋጋ የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት ግድ ይላል፡፡ ሀገራችን
ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ እጅግ ደካማ የፋይናንስ ስርዓት ካላቸው
ሀገራት በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ናት፡፡ የተቆጣጣሪ
አካሉ ማለትም የብሄራዊ ባንክ አቅም ውሱንነት፣የፋይናንስ
አገልግሎቱ በዋናነት የተንጠለጠለው በጥሬ ገንዘብ ስርዓት ላይ
መሆን፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ብቁና ተወዳዳሪ
አለመሆን፣የፋይናንስ ስርዓቱ አወቃቀር የኢንቨስትመንት
ባንኮች፣የካፒታልና ጠንካራ የገንዘብ ገበያ የሌሉበት መሆን
(money market)፣ የፋይናንስ ስርዓቱ አካታችና ተደራሽ
አለመሆን፣ የቁጥጥር ስርዓቱ ገዳቢ (restrictive) እና የውጭ
ካፒታል ፍሰትን የሚገታ መሆኑ በመሰረታዊነት የሚጠቀሱ
ችግሮች ናቸው፡፡
የሀገሪቱን የተዛባ የፋይናንስ ስርዓት ለመገንዘብ ይረዳ ዘንድ
የተወሰኑ መረጃዎችን መመልከት ተገቢ ነው። በ2012 ዓ.ም
ጥቅል ዓመታዊ ዋጋ ግሽበት ወደ 20 በመቶ ያደገ ሲሆን
የምግብ ዋጋ ንረትም ወደ 18 በመቶ ደርሷል፡፡ ለዋጋ ግሽበቱ
የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ መደረጉ አስተዋጽኦ
አድርጓል፡፡ የብር ከዶላር አንጻር እንዲዳከም የተደረገው
48 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !