Page 52 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 52
አብን
ሊደግፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ የመንግስት የልማት
ድርጅቶች ሊከፍሉ ከሚችሉት በላይ የውስጥና የውጭ ብድር
ጫና አለባቸው፡፡ በተለይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲወስዱ
የተደረገው የሃገር ውስጥ ብድር ሳይመለስ እየተቆለለ መሄዱ
የሃገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ለከፍተኛ የዕዳ ጫና የዳረገና
በተዘዋዋሪ መንገድም ህዝቡን ለኑሮ ውድነት የዳረገ ነው፡፡
2.7. የሃገራችን ኢኮኖሚ በእጅጉ በተዛባ የወጪ እና የገቢ
ንግድ ሚዛን እየተጠቃ ይገኛል
የሃገራችን የወጪ ንግድ ያለፉት ሰላሳ ዓመታት ችግር በጣም
ጥቂት በሆኑ የወጭ ንግድ ምርቶች ላይ የተመሰረተ መሆኑና
በዚህም ምክንያት ለውስጥና ለውጭ ተፅዕኖዎች የተጋለጠ
መሆኑ ነው፡፡ የኤክስፖርት ምርት የምናቀርብላቸው ሀገሮች
ውስን መሆናቸው ሌላው የዘርፍ ችግር ነው፡፡
ባለፉት ሳላሳ ዓመታት የወጪ ንግድ ገቢያችን ከውጭ
ለምናስገባው እቃና አገልግሎት የሚያስፈልገንን ወጪ
ለመሸፈን ያለው አቅም በየጊዜው እያሸቆለቆለ በመሄድ ላይ
ይገኛል፡፡
በመሆኑም ሀገራችን የሚያስፈልጋትን የውጭ ምንዛሬ
በአብዛኛው የምታገኘው ከብድርና እርዳታ እንጅ ራሷ
ከምታፈራው የወጪ ንግድ ገቢ አይደለም፡፡ የሃገራችን የገቢ
ንግድም እንደዚሁ በችግሮች የተተበተ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት
የገቢ ንግድ የሚያስወጣው ወጨ ከወጭ ንግዱ ገቢ ስድስት
እጥፍ በላይ መሆኑ፣ ኢኮኖሚውን ለከፍተኛ ችግር
አጋልጦታል፡፡ ለረዥም ዓመታት እየቀጠለ የመጣው የንግድ
50 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !