Page 56 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 56
አብን
ጨምሮ የሚመረተው የምርት መጠን (አቅርቦት) ምርቱን
ለመሸመት በገበያ ውስጥ ካለው ፍላጎት ጋር ተጣጥሞ
አያውቅም፡፡ አቅርቦት ከፍላጎት በታች ሆኖ በቆየባቸው
ዘመናት ሁሉ የዋጋ ንረት እንዳሁኑ ዘመን በከፍተኛ ደረጃ
ንሮ አያውቅም፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የዋጋ ንረት መጠን በከፍተኛ
ደረጃ እየናረ ለመሄዱ የአቅርቦት ዝቅተኛነትን ብቻ
በምክንያትነት ማቅረብ የሚያስኬድ አይሆንም፡፡
በተለይ በህወሓት ዘመን መንግስት ከአቅም በላይ በማቀድ
የበጀት ጉድለቱን ከብሄራዊ ባንክ በመበደር ያሟላ ነበር፡፡
ገንዘብ ወጪ የተደረገባቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶችም
በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ወደ ምርት ሊገቡ ስላልቻሉ እና
በሙስና የሚዘረፈው ሃብት ከፍተኛ ስለነበር፣ በገበያ ውስጥ
የተረጨው ገንዘብ በገበያ ውስጥ ካለው ምርት ጋር
የተመጣጠነ አልነበረም፡፡ ስለሆነም ረዘም ላለ ጊዜ በየጊዜው
እየታተመ ወደ ገበያ የሚረጨው ገንዘብ ምርትን በገበያ
ውስጥ ለማዘዋወር ከሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በላይ
ነበር፡፡ ገበያው ከፍተኛ መጠን ባለው ገንዘብ እንጅ በበቂ
ምርት ባለመደገፉ በተከታታይ ዓመታት እያሻቀበ የሚሄደውን
የዋጋ ንረት ለማስከን አልተቻለም፡፡
መንግስት በዘገበው መሰረት ከ1995 -2010 ባሉት 16 የበጀት
ዓመታት የነበረውን ዓመታዊ አማካይ የዋጋ ንረት 15%
መሆኑ፣ በተለይ ባለፉት ሶስት ዓመታት የነበረው እና
አሁንም ያለው አማካይ የዋጋ ንረት ከ15% በእጅጉ ከፍ ያለ
መሆኑን ያመለክታል፡፡
54 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !