Page 61 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 61

አብን


              እየተባባሰ  ይገኛል፡፡  የሀገሪቱ  የትምህርት  ስርዓት  በሃሰት

              ትርክት ላይ ለተመሠረተ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ እንጅ
              ከሀገሪቱ  የልማት  ፍላጎት  ጋር  ያልተጣጣመ  በመሆኑ፣
              ከትምህርት  ቤት  የሚወጡ  አብዛኛዎቹ  ወጣቶች  ሥራ  ፈት
              ሆነው  የቤተሰብ  እና  የሃገር  ሸክም  ከመሆን  የተሻለ  ነገር
              ሊገጥማቸው             አልቻለም፡፡           ያሉት          መረጃዎች
              እንደሚያመለክቱት  በሃገራችን  በአሁኑ  ጊዜ  ለሥራ  ከደረሱ
              ወጣት  ዜጎች  መካከል  ወደ  50%    የሚጠጋው  ሥራ  አጥ
              ነው፡፡  ከተሞች  አካባቢ  ያለው  የሥራ  አጥ  መጠን  ከጠቅላላ

              የከተማ ነዋሪው መካከል ከ45% በላይ ነው፡፡ በገጠር የአካባቢ
              መጎዳትን  የሚከለክል፣  የመሬትን  ምርታማነት                      ለማሳደግ
              የሚያስችል የግብርና ስትራቲጂ እንዳይኖር፣ መሬት የፖለቲካ
              መሳሪያ እንጅ የኢኮኖሚ ሃብት ማፍሪያ እንዳይሆን በመደረጉ
              በተለያየ ምክንያት ከመሬት ይዞታው የተነቀለ ከፍተኛ ቁጥር
              ያለው  የገጠር  ሕዝብ  በሥራ  ፈትነት  እና  ሥራ  አጥነት

              ስለተጎዳ፣  በድህነት  ሰንሰለት  ተተብትቦ፣  ገጠሩ  ሊያኖረው
              ባለመቻሉ  ወደ  ከተሞች  በመፍለስ  ወይም  እራሱን  ለከፍተኛ
              አደጋ እያጋለጠ ውቅያኖሶችን ለማቋረጥ ተገዷል፡፡

             2.12.  አሁን በሀገራችን የሚተገበረው የታክስ ፖሊስ ችግሮች
                    መገለጫዎችና አንድምታቸው
                  ግብር       ሰብሳቢው        ተቋም      ግብርን      የሚጥልበት፣

                    የሚሰበስብበት  እና  የሚያስተዳደርበት  ስርዓት  ኃላቀር
                    ነው፡፡  እንደሚታወቀው  ኢትዮጵያ  የግብር  ስርዓት
                    ከጀመረች  በርካታ  ዘመናትን  ብታስቆጥርም  በፖሊሲ
                    ችግር  ምክንያት  እስካሁን  አሰልቺ፣  ተገማች  ያልሆነ፣
                    ውስብስብ፣  ግብር  ከፋዮችን  የሚያማርር  እና  ንግድና

               59   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   56   57   58   59   60   61   62   63   64   65   66