Page 60 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 60
አብን
ጋር ያልተገናዘበ መሆኑ የዋጋ ንረቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ
እንዳደረገ ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከአስራ
አምስት ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ ህዝብ መሃል ግማሽ
ያህሉ ከድህነት ወለል በታች ባለ የኑሮ ደረጃ የሚኖር ነበር፡፡
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከፖለቲካው አለመረጋጋትና
ከኦኮኖሚው መቀዛቀዝ ጋር ተያይዞ ይኸ አሃዝ ከ60 በመቶ
በላይ እንደሆነ ይገመታል፡፡ በደቡብ እና ምስራቅ እስያ
ሀገሮች ከሃምሳ አመታት በፊት የነበረውን ወደ 35%
የሚጠጋ ከድህነት ወለል በታች የነበረ የህዝብ መጠን በሃያ
ዓመታት ብቻ ወደ 10% ለማውረድ ችለዋል፡፡ በእኛ ሁኔታ
ግን የእስያ ሀገሮች በየአመቱ ባደጉበት ፍጥነት በየአመቱ
እድገት ማስመዝገብ ብንችል እንኳ፣ እነሱ ከሃምሳ ዓመታት
በፊት ወደ ነበሩበት መጠን ለማድረስ በቀላሉ ሃምሳ አመታት
ገደማ ይወስድብናል፡፡ ከዚህ ባነሰ ጊዜ ከሃገራችን ፍፁም
ድህነትን ለማስወገድ ቢያንስ ለሃያ እና ሃያ አምስት ዓመታት
በተከታታይ እና በየዓመቱ 8% የኢኮኖሚ እድገት
ማስመዝገብ ይጠበቅብናል በተጨማሪ በፕሮፖጋንዳ ሳይሆን
በተጨባጭ በየዓመቱ ሁለት ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ
እድል መፍጠር ያስፈልጋል፡፡
2.11. ሥራ አጥነት
የሃገሪቱ የልማት ፖሊሲ ኢንቨስትመንትን የሚያደፋፍር እና
አደዲስ የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ የሚያበረታታ
ባለመሆኑ ያለው የሥራ አጥነት መጠን በከፍተኛ ደረጃ
58 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !