Page 59 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 59

አብን


                    የኢትዮጵያ  ንግድ  ባንክ  በቅርቡ  የጨመረው  የወለድ

                     መጠን  በአጠቃላይ  ኢኮኖሚ  እንቅስቃሴ  ላይ  ተፅዕኖ
                     አለው፡፡  በተለይ  ደግሞ  የኮንድሚንየም  ቤቶችን
                     በብድር  የገዙ  ነዋሪዎች፣  የወለድ  መጠን  ከ7  ወደ  9
                     እና ከ9 በመቶ በላይ መጨመሩ፣ የቤት ኪራይ ዋጋ
                     እንዲጨምር  አድርጓል፡፡  ይኸም  ለኑሮ  ውድነት
                     መባባስ ሌላው ምክንያት ነው፡፡
                    የኮሮና  ወረርሽኝ  ወደ  ሃገራችን  ከገባ  ግዜ  ጀምሮ
                     ከውጭ  ተገዝተው  እንዲገቡ  የተደረጉ  እንደ  ስንዴ፣

                     መድሃኒት  እና  ዘይት  ባሉ  ሸቀጦች  ላይ  የተጣለው
                     ቀረጥ  መጨመር  ለዋጋ  ንረቱ  ይበልጥ  አስተዋጽኦ
                     አድርጓል፡፡
                     በትግራይ  ጦርነት  ምክንያት  በተፈጠረው  የምግብ
                     እህል  እጥረት  70  በመቶ  ያህሉን  እጥረት መንግስት
                     ለመሸፈን መገደዱ ለመሰረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ መናር

                     ተጨማሪ ምክንያት ነው፡፡
                    የውጭ ወረራ ስጋት እና ከምርጫ በኋላ ያለው ስጋት
                     በገበያ  ሊይ  የሚኖርን  እምነት  በመቀነስ  ለዋጋ  ንረት
                     መጨመር የተወሰነ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

             የዋጋ  ንረትን  ለመከላል  ዘላቂ  መፍትሄው  የዋጋ  ቁጥጥር
             ማድረግ  ሳይሆን  የምርት  መጠንን  መጨመር  ቢሆንም፣
             ሌላውና       የአጭር       ጊዜ     መፍትሄ       የሚሆነው         በምርት

             ያልተደገፈን ጥሬ ገንዘብን በገበያ ውስጥ ከመርጨት መቆጠብ
             ነው፡፡ ማለትም የገንዘብ አቅርቦቱ እድገት ከኢኮኖሚው እድገት




               57   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   54   55   56   57   58   59   60   61   62   63   64