Page 66 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 66

አብን


              በጥራት  ስለመገንባቱ  ከተሰጠው  ትኩረት  ጋር  የሚመጣጠን

              አልሆነም፡፡፡፡

              የዚህ  ዘርፍ  ሌላው  ዓይነተኛ  ድክመት  ወጪ  የሚመደበው
              መንግስት  ከሚከተለው  የዘውግ  ፖለቲካ  ጋር  በተገናዘበ
              መልኩ  እየሆነ  በመምጣቱ፣  ከኢኮኖሚ  አዋጭነት  ሳይሆን
              ከፖለቲካ  አዋጭነት  አንፃር  የሚመዘን  በመሆኑ፣  የሃገር

              ሃብት ያለ አግባብ የሚባክንበት ዘርፍም ሊሆን በቅቷል፡፡

             3.4.   የተዳከመ የማህበራዊ ዋስትና ስርዓት

              በግል  ዘርፍ  የተቀጠሩ  ሰራተኞች  ሙሉ  በሙሉ  በማህበራዊ
              ዋስትና  ሽፋን  ሊገቡ  ያልቻሉበት  ሁኔታ  አንዱ  በማህበራዊ
              ዋስትና  ዘርፍ  ያለ  ተግዳሮት  ነው፡፡  በህመም፣  በአደጋ፣

              በእድሜና  በመሣሠሉት  የራሳቸውን  ህይወት  መምራት
              ላልቻሉ  ዜጎች  ማለትም  ለአካል  ጉዳተኞች፣  ወላጅና  አስዳጊ
              አልባ  ለሆኑ  ሕፃናት፣  ለጦር  ጉዳተኞች  እና  ብሔራዊ
              ግዳጃቸውን የተወጡ ዜጎች በማበራዊ ዋስትና ስርዓት ሊሸፍኑ
              የሚችሉበት  ሁኔታ  ያለመኖር፣  የሃገሪቱን  ሃብት  ማህበራዊ
              ፍትህን  በተመረኮዘ  ሁኔታ  ለማዳረስ  ያለመቻል  ችግር

              እንደሆነ  እሙን  ነው፡፡  የጡረተኞች  አበል  በየጊዜው  እያደገ
              ከሚሄደው  የዋጋ  ንረት  እና  የኑሮ  ወድነት  ጋር  እንዲገናዘብ
              ያለመደረጉ፣  ለሃገራቸው  ግዴታቸውን  የተወጡ  ዜጎች
              በሚደክሙበትና  እርዳታ  ሊደረግላቸው  በሚገባበት  ጊዜ
              ለችግር  እንዲጋለጡ  ተደርጓል፡፡  ይህ  መፍትሄ  ሊፈለግለት
              የሚገባ ሃገር አቀፍ ችግር ነው፡፡




               64   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   61   62   63   64   65   66   67   68   69   70   71