Page 70 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 70
አብን
የተደረጉ ናቸው፡፡ ሁሉም የድርድሩ አካላት የየራሳቸውን
መነሻዎች አቅርበው ውይይትና ድርድር ተደርጎ ፍትሃዊ
አማካኝ ላይ የሚደረስ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሆኖም ከመነሻው
ውይይቱና ድርድሩ የሚመራባቸውን ደንቦች በደንብ መቅረጽ
ያስፈልጋል፡፡ ድርድሩ በአንድ ሀገር ውስጥ ወደፊት ሊያሰራና
ሊያራምድ የሚችል ስርአት የመገንባት ሂደት መሆኑን ሁሉም
ባለድርሻ አካላት መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡
ሀገራችን ለረጅም ዘመን በቆየ የፖለቲካ ምስቅልቅል ውስጥ
መቆየቷንና አሁንም ቢሆን አደጋው እየተባባሰ መምጣቱን
መካድ አይገባም፡፡ ስለሆነም የችግሮቹ አይነተኛ ምንጮች
በመረጃና በእውቀት ተለይተው መቀመጥ አለባቸው፡፡ በግብ
ደረጃ የተያዙ የታክቲክ ጉዳዮች በቅጡ ተፈትሸው ተለዋጭ
መርኆችን ለመንደፍ መስማማት ያስፈልጋል፡፡ የሀገርን
አንድነትና ሉዓላዊነት ጉዳዮች ያለቅድመሁኔታ የሚከበሩ እንጅ
እንደሁኔታው የሚታዩ ሊሆኑ አይገባም፡፡ ስለሆነም ስርዓት
ለመገንባት ታስቦ በተከፈተው የድርድር መድረክ ውስጥ
ያልተገሩ ንጥል ፍጆታዎችን በማቅረብና ተቀባይነት የማያገኙ
ከሆነ ከመድረኩ መውጣት የሚቻልበት ሁኔታ ሊፈቀድ
አይገባም፡፡ ቅቡል የፍልስፍና መሰረት የሚኖረው
ሕገመንግስታዊ የዴሞክራሲ ስርአት እንጂ ለዜግነት መብቶች
ፍጹም የሆነ እውቅናን የሚነፍጉ ብሄርና ሀይማኖት ተኮር
ፖለቲካ ሊሆን አይችልም፡፡ ግለሰቦች መብቶችና ህልውና
የሚኖራቸው በብሄር ወይም በሀይማኖት ማዕቀፎች ውስጥ
ሲሆኑ ብቻ ነው የሚል የፖለቲካ እሳቤ ኋላ ቀር ነው፡፡
ከባህልና ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ የሚነሱ የተረጋገጡና
በመርህ የሚደገፉ መብቶች ተገቢውን እውቅናና ከለላ ማግኘት
68 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !