Page 72 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 72

አብን


             የፖለቲካ  እሳቤ  ስጋና  ደም  የለበሰው  በህገ-መንግስቱ  መግቢያ

             (preamble)  እና  ህገመንግስቱ  አንቀፅ  8  ድንጋጌ  እንደሆነ
             በፅኑ  ያምናል፡፡  ስትራቴጂክ  በሆነ  እይታ  ስንቃኘው  የህገ-
             መንግስቱ  መግቢያ  እና  አንቀፅ  8  አጠቃላይ  ህገመንግስቱና
             የሀገራችን መሰረታዊ የፖለቲካ ችግሮች የቆሙባቸው አምዶች
             መሆናቸውን እንረዳለን፡፡


             በብሄር ማንነትና ተያያዥነት ባላቸው የመብት ጉዳዮች ዙሪያ
             ካሉ  አለም  አቀፍ  ስምምነቶችና  አለም  አቀፍ  የባህል  ህግ
             መርሆዎች  በተጣጣመ  መልኩ  ጥበቃ  የሚደረግላቸው
             ይሆናል፡፡      የመንግስትና         የሀይማኖት         መለያየት       መርህ
             ህገመንግስታዊ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን የሀይማኖት ነጻነትን
             በተመለከተም  አለማቀፉ  የመብት  ድንጋጌዎችና  ልማዶችን
             መሰረት  ባደረገ  መልኩ  እውቅናና  ከለላ  የሚሰጥ  ይሆናል፡፡
             አሁን  በሚታየው  የሀገራችን  ተጨባጭ  ሀይማኖት  የፖለቲካ

             ማደራጃ ወደመሆን እየተሸጋገረ ሲሆን በማህበረሰቦች መካከል
             የቅራኔና የግጭት ምንጭ ለመሆን በቅቷል፡፡ ለዚህ ጉዳይ ልዩ
             ትኩረት  ተሰጥቶ  ወሳኝና  አፋጣኝ  መፍትሄ  የማይፈለግ  ከሆነ
             በብሄር  ክፍፍል  ምክንያት  እየተናጠች  ያለችውን  ሀገር
             መወጣት  በማትችለው  ድርብርብ  አደጋ  ውስጥ  እንደማስገባት
             ይቆጠራል፡፡


             በተለይ  የሀይማኖት  ችግር  በሀገራዊ  ማእቀፍ  የመርህና
             የመብቶች  ጉዳይ  ቢሆንም  በተደጋጋሚ  በልምድ  እንደታየው
             ከመልክዓ ፖለቲካና አለማቀፍ ድፕሎማሲና የሀይል አሰላለፍ
             ጋር  ቁርኝት  ያለው  በመሆኑ  ከፍተኛ  ጥንቃቄና  ትኩረትን




               70   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   67   68   69   70   71   72   73   74   75   76   77