Page 77 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 77

አብን


             መንግስት  ጉዳዮች  ፍ/ቤት  እንዲቋቋም  ይደረጋል፡፡  የፌደራል

             መንግስት  አካላት  ስልጣንን  ተግባር  ዝርዝር  በህገ  መንግስቱ
             ውስጥ  የሚካተት  ሆኖ፣  በስልጣን  መባለግን  ለመቆጣጠርና
             የህግ  የበላይነትን  ለማረጋገጥ  በህግ  አውጭው  አስፈፃሚውና
             ተርጓሚው  መካከል  የሚኖረው  ግንኙነት  እያዳንዱ  አካል
             ከተሰጠው  ተግባርና  ኃላፊነት  እንዳያልፍ  የሚያስችል  ጠንካራ
             የቁጥጥርና  ተማዝኖ  (check  and  balance  )  አሰራር
             ይዘረጋል፡፡


             1.2.   የራስ-ገዝ አድያማት ስልጣንና ተግባር

          ኢትዮጵያ  የሚኖራት  የፌደራል  ስርዓት  አወቃቀር  የኢትዮጵያን
          ታሪክ፣ አሰፋፈር፣ ባህላዊ እሴቶች፣ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥን፣
          የአስተዳደር  አመችነትን፣  የኢኮኖሚ  እድገት  ማሳለጥን፣  መሬት

          ገበያና የተፈጥሮ ሃብቶች ድልድል፣ የህዝቡን አብሮነትና ባህላዊ
          ትስስር  ማጎልበትንና  የአገሪቱን  አንድነት  መጠበቅን  መሰረት
          ባደረገ  ሁኔታይሆናል፡፡  የፌደራል  አድያምት  አወቃቀር  እና
          አደረጃጀት  ዝርዝር  በህገ  መንግስቱ  የሚወሰን  ይሆናል፡፡
          የፌደራሉና  የአድያም  መንግስታት  የሚኖራቸው  የተናጠልና
          የጋራ  ስልጣን  በህገ  መንግስቱ  በዝርዝር  የሚገለጽ  ይሆናል፡፡
          የፌደራል  አድያማት  የህዝባቸውን  ኢኮኖሚያዊና  ማህበራዊ
          እድገት            ለማረጋገጥ፣               ሰብአዊ             መብቶችን

          ለማስከበር፣ ቋንቋና ባህላቸውን  ለማሳደግና  የህዝቡን  ሰላምና
          ደህንነት  ለመጠበቅ  የሚያስችሉአቸው  የህግ  አውጭ  ህግ
          አስፈፃሚና  ህግ  ተርጓሚ  አካላት  ይኖሩዋቸዋል፡፡                      የፌደራል
          አድያማት  መንግስታት  ልዩ  ልዩ  አካላት  ስልጣን፣  ተግባርና
          ግንኙነት የፌደራሉን ህገ መንግስት መሰረት በማድረግ አድያማት


               75   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   72   73   74   75   76   77   78   79   80   81   82