Page 79 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 79
አብን
ሰብዓዊ መብት የሚጠብቅና ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ማንኛውም ግለሰብ ከህግ አግባብ ውጭ መብቱን፣ ነፃነቱን፣
ንብረቱን እና ጥቅሞቹ እንዳይነኩ የህግ ጥበቃና ዋስትና ያገኛል፡፡
የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ተደራሽነት
ያላቸው የፍትህ አካላት በየደረጃው ይቋቋማሉ፡፡ በህዝብ
ተሳትፎና ነፃ ምርጫ የሚፀድቀው ህገ መንግስት የሁሉም ህጎችና
መንግስታዊ ውሳኔዎች የበላይ ሆኖ ያገለግላል፡፡
1.5. የግለሰብ መሰረታዊ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች
በኢትዮጵያ የሚፈጠረው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የግለሰቦች
ሲቪል፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች የሚያረጋግጡበትና
የሚጠበቁበት ይሆናል፡፡ አብን የሚከተላቸው መሰረታዊ መብቶች
ህገ መንግስታዊ ጥበቃ እንዲያገኙ ይታገላል፡፡ በህይወት የመኖር
ሰብዓዊ ክብር፣ በግል ህይወት ጣልቃ አለመግባት፣ ንብረት
የማፍራትና የማስተላለፍ፣ በነፃነት የማሰብ፣ የሃይማኖት ነፃነት፣
ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት፣ በነፃነት
የመዘዋወር መብቶች ይረጋገጣሉ፡፡ የህግ የበላይነት በተረጋገጠበት
ስርዓት ውስጥ ምንም አይነት የጎሳ፣ የዘር፣ የጾታ የእድሜ
እንዲሁም በአካል ጉዳተኝነት ላይ የተመሰረተ አድልዎ
ተቀባይነት የለውም፡፡ የተለያዩ ማህበረሰቦች ባህላዊ እሴቶችና
መብቶች ህጋዊ ዋስትና እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ በተለይም
የተለያዩ ማህበረሰቦች ባህላዊ ቁሳቁሶችና እሴቶች እንዲከበሩና
እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡ የግለሰቦችንና የማህበረሰቦች መብቶች
ለማስከበር በየደረጃው የሚቋቋሙት የመንግስት አካላት ሁሉም
ዜጎች እኩል እድሎች እንዲያገኙ፣ ኑሮአቸው እንዲሻሻል፣
ድህነትን መዋጋትና የሀብት ብክነትን በመዋጋት ፍትሃዊ
77 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !