Page 78 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 78

አብን


          በሚያወጡአቸው ዝርዝር ህጎች የሚወሰን ይሆናል፡፡ የአድያማት

          ህገ  መንግስታት  የፌደራሉን  ሕገ  መንግስት  በሚፃረር  መልኩ
          ሊዘጋጁ አይችሉም፡፡
          ፌደራላዊ  ስርአቱ  እንዲጠናከርና  እንዲጎለብት  ነፃ  ብሔራዊ
          የምርጫ ኮሚሽን፣ ብሔራዊ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የአሰራር
          ነፃነት ያለው ብሔራዊ ባንክ፣ ፣ ብሔራዊ የደህንነት ም/ቤት እና
          ብሔራዊ የመከላከያ ደህንነት ም/ቤት እንዲቋቋሙ ይደረጋል፡፡


             1.3.   ብሔራዊ አንድነትንና መቀራረበን የመፍጠር ኃላፊነት

          የፌደራል መንግስት ብሔራዊ አንድነትና መቀራረብን ለመፍጠር
          እና የበለጠ የማጠናከር ኃላፊነቱን ለመወጣት፣ የህዝቦች ሸቀጥና
          አገልግሎቶች  በመላ  ሃገሪቱ  በነፃነት  የሚንቀሳቀሱበትን፣  ሁሉም
          የአገሪቱ ዜጎች በሁሉም አካባቢዎች ያለምንም ገደብ በእኩልነትና
          ያለ  አድሎ  የሚኖሩበትን፣  ያፈሩት  ሃብት  የህግ  ከለላ  አግኝቶ
          የሚከበርበት፣          ቋንቋን፣       ባህልና       ሃይማኖትን         የተሻገሩ

          አደረጃጀቶችና  የሲቪል  ማህበራት  እንዲፈጠሩ  ከፍተኛ  ሚና
          ይኖረዋል፡፡  ይህንን  አላማ  ከግብ  ለማድረስ  መንግስት  የሲቪል
          ማህበረሰብ        ተቋማትን፣         የሰራተኛና        ሙያ       ማህበራትን፣
          መንግስታዊ  ያልሆኑ  ድርጅቶችን፣  የረድኤት  ድርጅቶችን
          እንዲቋቋሙ ያበረታታል፤ ያግዛል፡፡


             1.4.   የህግ የበላይነትና የፍትህ አካላት ሚና

          በኢትዮጵያ  የሚኖረው  የፖለቲካ  ስርዓት  የህግ  የበላይነት
          የተረጋገጠበት ይሆናል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ ወይም መንግስታዊ
          አካል  ለህግ  የበላይነት  ተገዥ  ይሆናል፡፡  መንግስት  የሚመራበት
          ህግ ግልጽ የሆነ፣ አስቀድሞ በህግየወጣና የግለሰቦችን መሰረታዊ


               76   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   73   74   75   76   77   78   79   80   81   82   83