Page 76 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 76

አብን


             ያስፈልጋል  የሚል  እምነት  አለው፡፡  በመሆኑም  ብሄራዊ

             ውይይት  እና  የልሂቃን  ድርድር  መድረኮችን  በማመቻት
             የሕገመንግስት         አርቃቂ       ኮሚሽንን       በአዋጅ       እንዲቋቋም
             ያደርጋል፡፡

             1.3.    የህዝብ  የስልጣን  ባለቤትነት  እና  ዲሞክራሲያዊ
                    ስርዓት


          በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት የመላው
          የአገሪቱ  ሕዝብ  ይሆናል፡፡  የህዝብ  ሉዓላዊ  የስልጣን  ባለቤትነት
          የሚረጋገጠው  ነፃ፣  ፍትሃዊ  እና  ዲሞክራሲያዊ  በሆነ  የምርጫ
          ሂደት የሚፈልገውን ፓርቲ መርጦ ለሥልጣሠን በማብቃት እና፣
          ክንውኑ ሳያስደስተው ሲቀር ደግሞ በሚቀጥለው ምርጫ በድምፁ
          በመቅጣት ለማውረድ ሲችል ነው፡፡



             1.1.    የፌደራል መንግስት አካላት የስልጣን ክፍፍልና
                    የርስ በርስ ቁጥጥር  (Check  and  Balance)

              የፌደራል  መንግስቱ  ህግ  አውጭ፣  አስፈፃሚ  እና  ተርጓሚ

             አካላት ይኖሩታል፡፡ የህግ አውጭው መላው ህዝቡን የሚወክል
             ተወካዮች  ም/ቤትና  የራስ  ገዝ  አድያማት  መንግስታትን
             ጥቅሞች  የሚወክል  የህግ  መወሰኛ  ም/ቤት  ይኖሩታል፡፡
             የሪፐብሊኩ  ፕሬዘዳንት  የርእሰ  ብሔርና  ርዕሰ  መንግስትነት
             ስልጣን ይኖሩታል፡፡ የፌደራል መንግስቱ በየደረጃቸው ስልጣን
             የሚኖራቸው ፍ/ቤቶች የሚኖሩት ሆኖ የሪፐብሊኩ የመጨረሻ
             ፍርድ ሰጪ አካል የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይሆናል፡፡ በህገ

             መንግስታዊ  ጉዳዮች  ላይ  የመጨረሻ  ውሳኔ  የሚሰጥ  የህገ

               74   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   71   72   73   74   75   76   77   78   79   80   81