Page 69 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 69
አብን
መደንገግ በራሱ ዘላቂ እልባት ማምጣት እንደማይችል
በመገንዘብ በሂደት መሰረታዊ መርሆዎችን በማህበረሰቡ
ውስጥ በማስረጽ የዴሞክራሲያዊ ስርአትን ማጎልበት
ያስፈልጋል፡፡ ይህ የሚሆነው የዴሞክራሲ ባህልን በመገንባት
ሲሆን በተግባር ሁሉም አካላት በሕገመንግስቱ የተጻፉትን ብቻ
ሳይሆን የታሰቡትንና የተመላከቱትን መርሆዎች /spirit of
the constitution/ በጽኑ በመከተል ጭምር ይሆናል፡፡ በዚህ
ረገድ ጥቅል የሆኑ መርሆዎችን በዝርዝር የተደነገጉ የግለሰብና
የቡድን መሰረታዊ መብቶችን፣ የስልጣን ክፍፍሎችን፣
የዳኝነት ስርአቱን ባከበረ መልኩ ግንኙነቶችንና ክንውኖችን
ለማሳለጥ የህግ የበላይነት መርህ በአግባቡ መጠበቅ
ይኖርበታል፡፡
አሁን በስራ ላይ ያለውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገመንግስት
በተመለከተ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) ዝርዝር
ምልከታዎቹን በተለያዩ አጋጣሚዎች በይፋ ሲገልጽ መቆየቱ
ይታወሳል፡፡ በሕገመንግስቱ ላይ የተደራጀ የግምገማና የትችት
ስራውን በሰነድ መልክ አዘጋጅቷል፡፡ ንቅናቄያችን
ሕገመንግስቱን ለመለወጥ በሚከፈተው ሀገራዊ መድረክ ላይ
ይዞት የሚቀርበውን አማራጭ የሕገመንግስት ሰነድ ከቀረጸ
ቆይቷል፡፡
ከላይ ለማመላከት እንደተሞከረው ሕገመንግስቱ የድርድር
ውጤት እንደመሆኑ መጠን በእኛ በኩል የሚቀርበው ረቂቅ
ሀሳብ የመድረኩ አንድ ግብዓት ሲሆን አብን ያነገባቸውን
አማራዊና ሀገራዊ ራእዮች ለማሳካት ጠቃሚ ናቸው ብሎ
በጥናት ያረጋገጣቸውን ጉዳዮች እውን ለማድረግ ታሳቢ
67 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !