Page 51 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 51
አብን
የውጭ ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በሚል ምክንያት
ቢሆንም በውጭ ዘርፍ ያሳየነው ውጤት ግልጽ አይደለም፡፡
መንግስት የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ሲያደረግ የዋጋ
ግሽበት እንዳይጨምር በፋይናንስ ዘርፉ ጠበቅ ያለ ፓሊሲ
ተግብሯል፡፡ከነዚህም መካከል የንግ ድባንኮችን በብሔራዊ ባንክ
የሚያስቀምጡትን መጠን ከነበረበት 5 በመቶ ወደ 7 በመቶ
የማሳደግ ስራ የተሰራ ሲሆን አማካይ የቁጠባ ወለድ መጠንም
ከ5.4 በመቶ ወደ 8 በመቶ እንዲሁም የብድር ወለድም ከ12.8
በመቶ ወደ 14.3 በመቶ እንዲያድግ እንዲሁም የብድር ጣራ
የመወሰን ስራም ተሰርቷል፡፡ይህን በማድረግም የገንዘብና
የብድር አቅርቦት ዕድገት የተገደበ እንዲሆን አድርጓል፡፡
ይሁን እንጅ የዋጋ ግሽበቱም ሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ
አጀግ እየከፋ እንጅ ጤናማ እና የተረጋጋ መሆን አልቻለም፡፡
ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የሃገሪቱ የገንዘብ ድርጅቶችና
አስተዳደራቸው ዘርፉን ከሌሎች አምራች ዘርፎች ማለትም
ከግብርና፣ ከኢንዱስትሪ እና ማዕድን/ እንዲሁም ከአገልግሎት
ዘርፉ ጋር ከማስተሳሰር ይልቅ፣ ቀደም ሲል ህውሓት በአሁኑ
ጊዜ ደግሞ የኦሮሞ ብልጽግናን የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈፀሚያ
ሆነው እንዲያገለግሉ መደረጋቸው ይስተዋላል፡፡ ብሔራዊ ባንክ
በንግድ ባንኮች ላይ ያለው ገደብ የለሽ ጣልቃ ገብነት የግል
ባንኮችንም ሆነ የመንግስት ባንኮችን በእኩል አይን መምራት
ሲገባው ለመንግስት ባንኮች ያለው አድሎአዊ ምልከታ
ብሔራዊ ባንክ የገዥ ፓርቲው ፍላጎት ማስፈፀሚያ ሆኖ
ቆይቷል፡፡ መንግስት ሊሸከም ከሚችለው የብድር መጠን በላይ
ሲያበድር በመቆየቱ ኢኮኖሚው በተረጋጋ የፋይናንስ ምህዳር
49 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !