Page 53 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 53

አብን


              ሚዛን መዛባት የሃገሪቱን የውጭ ብድር ጫና በከፍተኛ ደረጃ

              እየጨመረው  በመሄድ  ላይ  በመሆኑ፣  የካቲት  ወር  2013
              በወጡ  መረጃዎች  መሰረት  በ2012  የሸቀጦች  የወጪ  ንግድ
              የገቢ  ንግድ  የወጪ  የመሸፈን  አቅሙ  ወደ  15%  አካባቢ
              መድረሱ  የሃገሪቱ  የንግድ  ሚዛን  ከፍተኛ  የአደጋ  ምልክት
              እየታየበት መሆኑ ይስተዋላል፡፡


              የሀገሮችንና  የግዙፍ  ኩባንያዎችን  የእዳ  ጫና  እንዲሁም  እዳ
              የመመለስ  አቅምን  በመገምገም  የምዘና  ደረጃ  በማውጣት
              በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁት ድርጅቶች መካከል ሙዲስ
              የተባለው  ተቋም  በግንቦት  ወር  2012  በወጣው  የምዘና
              ሪፖርት  የኢትዮጵያን  እዳ  የመክፈል  አቅም  ዝቅ  አድርጎ
              በመመዘን  ሀገራችንን  ከፍተኛ  የወጭ  እዳ  ካለባቸው  ሀገሮች
              ምድብ  ከቷታል፡፡  ፊች  (Fitch)    የተባለው  ተቋም  በካቲት
              2/2013  ባወጣዊ  ሪፖርት            ደግሞ  ኢትዮጵያ  የውጭ  እዳ

              የመክፈል  ግዴታቸውን  ሊያቋርጡ  ከሚችሉ  ከፍተኛ  ስጋት
              ከደቀኑ  ሀገሮች  ተርታ  የሚያስመድባት  (CCC)  ደረጃ
              ስጥቷል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ከግል የውጭ
              አበዳሪዎች  እዳ  የመክፈያ  ጊዜ  እፎይታና  ማራዘሚያ
              ለመጠየቅ ማቀዱን አመልክቷል፡፡

              ለዘላቄታው  የሃራችን  የገቢ  እና  ወጪ  ንግድ  ሚዛንም  ሆነ

              የመጠባበቂያ  ክምችት  ከውጭ  ብድርና  እርዳታ  ጥገኝነት
              መላቀቅ  እስከልቻለ  ድረስ፣  ኢኮኖሚው  ለከፍተኛ  ችግር
              መጋለጡ  እና  ይህም  ችግር  ወደ  ፖለቲካ  ቀውስ  ማምራቱ
              የማይቀር ነው፡፡


             2.8.   የኮሰመነ የመዋዕለ ነዋይ (ኢንቪስትመንት) መጠን
               51   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   48   49   50   51   52   53   54   55   56   57   58