Page 32 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 32
አብን
ፖለቲካ እና ርዕዮተ ዓለም አራማጆች መጠቀሚያ ለማድረግ
መሞከር ለሃገር አደጋ የሚጋብዝ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ እና በአባይ ሸለቆ ስትራቲጂያዊ
ቦታ ላይ የምትገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአካባቢው ያሉ
ታሪካዊ ተፃራሪዎቿ በውስጧ የተለያዩ እምነቶች መኖራቸውን
ለፖለቲካ ዓላማቸው መጠቀሚያ እንደሚያደርጉ በማወቅ
ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ
ይገባል፡፡
1.9.2. የውጭ ስጋቶች
1.9.2.1. የአባይ ተፋሰስ ፖለቲካ
የሃገራችን ዋነኛው የውጭ የስጋት ምንጭ “ከአባይ መርገምት”
(The Nile Curse) ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሱዳን እና ግብፅ
የህልውናችን መሰረት ነው የሚሉት ናይል ወንዝ 86%
የሚሆነውን የውሃ ድርሻ የሚሸፍነው የአባይ ወንዝ በመሆኑ
እና ሁለቱ ሀገራት የሚከተሉት ሚዛናዊ ያልሆነ እና ያልተገራ
የውሃ ባለቤትና አጠቃቀም ፍላጎት እያስከተለ ያለው ዘርፈ
ብዙ ጫና እና ጣልቃ ገብነት እጅግ ከፍተኛ የሆነ የውጭ
ስጋት ነው፡፡
30 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !