Page 28 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 28

አብን


             በባለቤትነት  መቆጣጠር  አለብን  በሚል  የመላ  ኢትዮጵያውያን

             መናኸሪያ  የሆነችውን  አዲስ  አበባን  ለብቻቸው  ለመቆጣጠር
             የሚያደርጉት ግፊት ነው፡፡

             ይህ  አካሄድ  የፌደራሊዝም  አሰራር  ሀሁን  ያላገናዘበ
             የስግብግብነት  እና  የተረኛነት  ፖለቲካ  አይነተኛው  መገለጫ
             ነው፡፡  ፌደራሊዝም  በየአካባቢው  የሚኖረው  ህዝብ  እራሱን
             በራሱ  የሚያስተዳድርበት  ስርዓት  ሲሆን፣  ከህዝብ  ውጭ
             በህዝብ  ላይ  የሞግዚት  አስተዳደር  መጫን  ፌደራላዊ  ሳይሆን

             አሃዳዊ  አስተዳደር  ነው፡፡  አብን  የአዲስ  አበባ  ነዋሪዎች
             ሊገረሰስ  የማይችለውን  ራሳቸውን  በራሳቸው  የማስተዳደር
             መብታቸው እንዲከበር ይታገላል፡፡ ዓለም በሚያውቀው ሁኔታ
             አዲስ አበባ የዘመናዊነት ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና ማገልገል
             ከጀመረች  ወደ  መቶ  ሰላሳ  ዓመታት  ተጠግቷል፡፡  ማንኛውም
             ኢትዮጵያዊ  አዲስ  አበባ  የጋራ  ከተማችን  ናት  የሚለውን

             የፖለቲካ  አቋም  ሊደግፍ  የሚገባው  አዲስ  አበባ  የተገነባችው
             ከመላ የኢትዮጵያ ማዕዘናት በመጡ የአሁኑ ጊዜ የአዲስ አበባ
             ነዋሪዎች  አያት  ቅድመ  አያቶች  ላብና  ጥረት  በመሆኑ  ብቻ
             አይደለም፡፡ ከበቂ በላይ የእውነተኛ ታሪክ በደጋፊነት ለማቅረብ
             በሚቻልበት  መልኩ  በኢትዮጵያ  ታሪክ  በመካከለኛው  ዘመን
             ማለትም ከ1382 እስከ 1531 ባለው የታሪክ ዘመን የአሁኒቷ
             አዲስ  አበባ  በተቆረቆረችበት  ቦታ፣  በራራ  በሚል  ስያሜ
             የተሰየመች  የመካከለኛው  ዘመን  የኢትዮጵያ  መንግስት  ዋና

             ከተማ፣  ባድማ  እና  ፍራስራሽ  ላይ  የተገነባች  በመሆኗም
             ጭምር ነው፡፡




               26   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   23   24   25   26   27   28   29   30   31   32   33