Page 27 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 27
አብን
የደቡብ አፍሪካ ልዩ ልዩ ነገዶች አሁን የሰፈሩበትን የአገሪቱን
አካባቢ የየነገዶቹ ነው የሚል አመለካከት ባለመያዛቸውና
ጥቁሩም ሆነ ነጩ እኩል የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ናቸው፣
ሀገሪቱም የሁሉም ነገድና ቀለም ህዝቦች የጋራ ሀገር ናት
በሚለው ፖለቲካ ጥቁሮችም ሆኑ ነጮች በመስማማታቸው
ነው፡፡
ሁሉንም የሃገራችን ነገዶች ኢትዮጵያዊነት ለሚቀበለው
ንቅናቄያችን ወደ ቀዳሚ ነገድ ትንተና መግባቱ ቢያሳዝነውም፣
የተዛባን የታሪክ ትርክት ማቃናቱ አስፈላጊ መሆኑን
ያምንበታል፡፡ ከትክክለኛውና የማያወላዳ ማስረጃ ሊቀርብ
ከሚችልበት የታሪክ ግንዛቤ ስንነሳ፣ የቱለማ ኦሮሞዎች ሸዋ
ከመምጣቸው በፊት ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት አዲስ
አበባን የከበባት የሸዋ ግዛት በአብዛኛው የአማራ ማህበረሰብ
በከፊል ደግሞ የጉራጌና ሌሎችም በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት
እንዲጠፉና እንዲዋጡ የተደረጉ የሃርላ፣ የጋፋት፣ የገንዝ፣
የወለቃ እና የማያ ማህበረሰቦች የሚኖሩበት ግዛት ነበር፡፡
በሃይል ከአፅመርስቱ የተፈናቀለውና በሰሜን ሸዋ አካባቢ
በገደላ ገደል ላይ እንዲንጠለጠል የተደረገው አማራው እንጂ
ኦሮሞው አይደለም፡፡ ትክክለኛው ታሪክ የሚያስገነዝበን
የተወረረው፣ ስልጣኔው የጠፋው፣ ባህሉ፣ እምነቱ፣ ማንነቱ፣
የተዋጠው፣ በገዛ ርስቱ ገባሪ የተደረገው አማራው እንጂ
ኦሮሞው አይደለም፡፡
ከሁሉም የባሰው የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም የነገድ
ፖለቲካን የማራመድ አካሄድ ጎልቶ የታየው የኦሮሞ ብልጽግና
እና ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔረተኞች በጋራ በመሆን አዲስ አበባን
25 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !