Page 86 - DINQ MAGAZINE SEPTEMBER 2020 EDITION
P. 86

ከገጽ 26 የዞረ


           ‹‹አባቴ ምንም አሉ ምንም ወደ ፈጣሪ ቤት መቼ          ‹‹ቆይ ጥያቄህ ምንድነው?›› ሽማግሌው በግርምት   ማሰቡንም፤ እራሴን አሳልፌ ልሰጣት ብፈልግም የእሷ
        እንደምመጣና ለምን እንደምመጣ አልመረምርም፡፡          ጠየቁ፡፡                                ብቻ እንድሆን እንደማትፈልግ ሳስብም እናደዳለሁ፡፡
        ጥያቄ ካለኝ እመጣለሁ፡፡››                                                          እሷ የምትለው ዛሬ መቼ እንደሆነ ልረዳው
                                                  ‹‹ጥያቄውን እንኳን ሳያውቁ ነዉ እንዴ መልስ     አልቻልኩም፡፡ እርስዎ ምን ይመክሩኛል አባቴ?››
           ‹‹ጥያቄ ካለህ ነው ወይስ መልሱን ከዓለም ፈልግህ    ይዘውልኝ የመጡት?›› አፈጠጠባቸው፡፡
        ካጣህ?››                                                                         ቀና ብሎ ባህታዊውን በጥያቄ አይን
                                                  ‹‹ልጄ፤ እኔ የእግዝያብሔር መልዕክተኛ ነኝ፡፡    ተመለከታቸው፡፡ ባህታዊው ሲያዩት ቆዩና የሚሉትን
           ‹‹ማለት?››                           አድርስ የተባልኩትን መልዕክት ማድረስ እንጂ          ለመስማት እንደጓጓ ሲረዱ ጉሮሯቸውን ጠራርገው፤
                                              ለማን?...ምን ሆኖ?...ለምን? እያሉ ፈጣሪን መጠየቅ የኔ
           ‹‹ለምሳሌ ትናንትና መጠጥ ቤት ከጓደኛህ ጋር       ሥራ አይደለም::››                             ‹‹ለዚህ እኮ ነዉ ፈጣሪ እንድትለያት የነገረህ››
        ተቀምጠህ ስታማክረው እሱ የምትፈልገውን መልስ                                               አሉት፡፡
        ቢሰጥህ ኖሮ ዛሬ ትመጣ ነበር?››                     ‹‹እሺ የኔ ጥያቄ ምን መሰለዎት…›› እጃቸውን ይዞ
                                              ሄዶ ድንጋይ ላይ አስቀመጣቸውና ከጎናቸው ቁጭ             ‹‹አባቴ እስኪ የፈጣሪን ይተውት እና እርስዎ እንደ
           ‹‹እየፈረዱብኝ ነዉ እንዴ አባቴ? አትፈረድ ይላል    ብሎ በተረጋጋ ድምጽ ማስረዳት ጀመረ፡፡             ራስዎት ምን ማድረግ እንዳለብኝ ንገሩኝ፡፡›› አላቸው፡፡
        እኮ መጽሐፉ፡፡››                                                                ባህታዊዉ በትዝብት ሲመለከቱት ቆዩና፤
                                                  ‹‹ይኸውልዎት አንዲት የምወዳት ሰብለወንጌል
           ባህታዊዉ በፈጣሪ ሥራ ተገርመው አናታቸዉን         የተባለች ጓደኛ አለችኝ፡፡››                       ‹‹ከፈጣሪ መልስ የኔ የአንድ ተራ ሰው መልስ
        ነቀነቁ፡፡ በውስጣቸዉ ‹አንተ ፈጣሪ ተፈጥሮህ ግሩም                                           ይሻልሀል ልጄ?››
        ነዉ፡፡ ቆይ ምንን ነው የምትመረምረው? አሁን ይሄ           ‹‹ሥሟስ መልካም ነበረ፡፡ ልጄ ያንተስ ሥም
        ልጅ ምኑ ነው የዋህ? በላ አይደል እንዴ!…ፈጣሪዬ ሆይ    ማነዉ?››                                   ‹‹አባቴ እንደዛ ማለቴ አይደለም፡፡ በቃ ፈጣሪ
        ይቅር በለኝ!...እኔ ያንተ መልዕክተኛ ነኝ፡፡ አንተ                                          ፈጣሪ ነው፡፡ ፈጣሪ ፍጹም ነው፡፡ ሰው ጎዶሎና ደካማ
        ያልከውን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡› አሉና ወደ ወጣቱ             ‹‹ሥሜንም አያውቁትም? እሺ ሠይፈ እባላለሁ -    ነው፡፡ ጎዶሎና ደካማ ሆኖ የፍጹምን መልስ ከመስማቱ
        ዞረው፤                                  ሠይፈ ገብርኤል….እና አባቴ ከሰብለ ጋር ተዋደን ነው    ይልቅ የጎዶሎው ያሳምናል፡፡››
                                              የተገናኘነው፡፡ አብረን ስንሆን ደግሞ በጣም
           ‹‹ልጄ እኔ አልፈረድኩብህም! እኔ ማነኝና ነው      ስለተጣጣምን ሁለታችንም ሲበዛ ደስተኞች ሆንን፡፡           ‹‹ቆይ ፍጹም የሆነው ፈጣሪ የምትፈልገውን ዓይነት
        በሰው የምፈርድ? እኔ የእሱ መልዕክተኛ ነኝ፡፡ እሱ      ነጭ ሹራብ ገዝቼ ሰጠኋት፡፡ ነጭ ሹራብ ገዝታ         መልስ ቢሰጥህ ኖሮ አልቀበልም ብለህ፤ ጎዶሎና ደካማ
        እንኳን አልፈረደብህም፡፡ ቤተ ክርስትያን ሳትመጣ        ሰጠችኝ፡፡ እሱ በጣም አመሳሰለን፡፡››             ወደሆነው ሰዉ ትሄድ ነበር?›› አሉት፡፡ ወጣቱ አቀርቅሮ
        እንኳን እዛው እምትጠጣበት ቤት መልስ ልኮልህ                                               ሲያስብ ቆየና፤
        ነበር›› አሉት፡፡                               ‹‹እና ምን ተፈጠረ ልጄ?››
                                                                                       ‹‹አላውቅም አባቴ፡፡ ሰውነት የሚባለው እንዲህ
           ‹‹አባቴ እኔ በዚህ ሰዓት ንቃ የሚለኝ ሰው            ‹‹ምን መሰለዎት አባቴ፤ ሰብለ አንዳችን ያንዳችን   መሆኑ መሰለኝ፡፡ አባቴ አሁን ከቻሉ መልስዎን
        አይደለም የምፈልገው፡፡ እኔ ምን ማድረግ እንዳለብኝ      ብቻ መሆናችንንና ፍቅረኛ ተብለን መጠራታችንን         ይስጡኝ፡፡›› አለና መልሶ አቀረቀረ:: ባህታዊው ትንሽ
        የሚነግረኝ ሰው ነው የምፈልገው::››               አትፈልገውም፡፡ ‹በቃ ዛሬን ብቻ እያሰብን           ሲያስቡ ቆዩና፤
                                              በመዋደዳችን እንደሰት:: ዛሬን ብቻ እንኑር፡፡ ፍቅር፣
           ‹‹ልጄ ንቃቱ እኮ ቢኖርህ ምን ማድረግ እንዳለብህ    ፍቅር እያልን እራሳችን በሠንሠለት አንጠፍር› ነው          ‹‹እሺ እንደ ራስህ ተናገር ካልከኝ እንደራሴ ሆኜ
        እራስህ ታውቅ ነበር፡፡ ደግሞ ማድረግ ያለብህን         የምትለው:: የሚገርመው አባቴ በፊት፣ በፊት ሴቶቹ      ልንገርህ…›› ባህታዊው ቀና ብለው ተመለከቱት፡፡
        ነግሬሀለው፡፡ ልጅቱን ተዋት፡፡ ነጭ ሹራቡን አውጥተህ     አልቀመስ አሉኝ እንጂ እንደዚህ ዓይነቱን ግንኙነት      እየሰማቸው እንደሆነ አረጋገጠላቸው፡፡ ቀጠሉ፤
        ወርውረዉ:: ደግሞ ቃሉ የኔ አይደለም፡፡ ፈጣሪ ነው      ስፈልገው ነበር የኖርኩት፡፡ አሁን ሳገኘው ግን
        እንደዛ ያለህ፡፡ ልጅቱ ቀድማህ መንገድህን ነጥቃ        የፈራሁት ደርሶ፤ የጠላሁት ወርሶ፤ እነዛ ስገፋቸው          ‹‹እንደኔ እንደኔ አንተ ምንም የዋህ አይደለህም፡፡
        ይዛብህ ከመሄዷ በፊት መንገድህን ይዘህ ሽሽ ብሎሀል      የነበሩት ሴቶች እንደሚያደርጉት ሰብለን ‹አሁን የት     የፈጣሪ ሥራ ግን ግሩም ነው:: ምንህን መርምሮ፣ በምን
        ፈጣሪ፡፡››                               ላይ ነዉ ያለነው? ግንኙነታችን ወስዶ የት ነው        መዝኖህ የዋህ እንዳለህ ማሰቡ ድንቅ ነዉ፡፡ ብቻ እሱ
                                              የሚያደርሰን? ነገ ምን ይዞልናል...› እያልኩ ነጋ ጠባ   ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ ቃሉ እውነት ነው፡፡››
           ‹‹አባቴ ቆይ መንገዴን ተሸክሜ በምን መንገድ       እጠይቃታለሁ፡፡ ሰሞኑን እግሯን ቀንሳለች፡፡
        አድርጌ ነዉ የምሸሸው?...ደግሞስ ወዴት ነዉ          ስልኬንም እንደ በፊቱ አትመልስም፡፡››                 ‹‹እውነት ነው አባቴ!›› አላቸው፤ ወደው ሳይሆን
        የምሸሸው? ሁሉም ቦታ እርሷ እኮ ነች ያለችው፡፡››                                           በግዳቸው የተቀበሉትን የዋህነቱን ለማስረገጥ፡፡
        በረጅሙ ተነፈሰ፡፡                               ‹‹ልጄ ዝሙት ሀጥያት እንደሆነ ታውቃለህ
                                              አይደል?››                                  ‹‹ልጄ የሰው ልጅ አመጸኛ ነው፡፡ ሰው በሰው ላይ
           ‹‹ቆይ ሳትሞክረው መንገድህን ተሸክመህ                                                ያምጻል፣ በእናት አባቱ ላይ ያምጻል፤ በእራሱ ላይ
        የምትሄድበት መንገድ እንደሌለህ እንዴት አወቅህ?            ‹‹እሱን የማያውቅ ማን አለ አባቴ?››         እንኳን ያምጻል፡፡ እሱ አልበቃ ሲለው ደግሞ፤ አልፎ፣
        ሳታየው ሁሉም ቦታ እርሷ እንዳለች እንዴት                                                 ተርፎ በፈጣሪውም ላይ ያምጻል፡፡ የምፈልገውን እንጂ
        ደረስህበት?››                                 ‹‹ባለማወቅና አውቀው ያወቁትን ተግባራዊ        የሚያስፈልገኝን አልፈልግም ብሎ ያምጻል፡፡ ቃሉን
                                              ባለማድረጉ መሀል ያለው ልዩነት ምንድነው ልጄ?››      የሚያውቅና በቃሉ የሚኖር ሰው እንኳን ከአመጻ
           ‹‹አባቴ፤ እሷ እኔ ውስጥ ነግሳ ነው ያለችው፡፡ እኔ                                       አይመለሰም፡፡ እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? ቆይ
        ካለሁ እሷ አለች፡፡ ሰዉ ከእራሱ መሸሽ ይችላል እንዴ?        ‹‹አባቴ ዛሬ ግን መች ነው?›› ከጠየቁት ጥያቄ   ልጅቱ ለምን ዛሬን ብቻ እንኑር ያለችህ ይመስልሀል?››
        ደግሞስ እግሬ እሷ ሆና ሳለች መንገድ መቀያየሩ ምን      የራሱ ሀሳብ በልጦበት ጥያቄአቸውን በጥያቄ መለሰ፡፡
        ጥቅም ይኖረዋል?››                                                                   ‹‹እሷማ ከዚህ በፊት በፍቅር ተጎድቻለሁ:: ድጋሚ
                                                  ‹‹ማለት ልጄ?›› ሽማግሌው ግራ ተጋቡ፡፡       በፍቅር ሥም መጎዳት አልፈልግም ነው የምትለው፡፡
           ‹‹ልጄ ጸሎትህን የሽኮኮ አታድርገው፡፡ ጥያቄ                                            እንደዚህ እንደተዋደድን እየተደሰትን እንኑር ነው
        ጠይቀህ መልስ ሲሰጠህ መልሱ እኔ እንደምፈልገው             ‹‹ዛሬን እንኑር፤ ዛሬን እንደሰት፤ ስለ ነገ አንጨነቅ   የምትለኝ፡፡ ሌላ ሴት ብትሆን እኮ ችግር የለውም ነበር፡፡
        አይደለም ብለህ መልሱን አልቀበልም አትበል፡፡          ትላለች፡፡ ወንጌሉም እንደዛ ይላል::››            እሷ ሆናብኝ እኮ ነው እንደዚህ የተጨነቅሁት፡፡››
        የምትፈልገውን ዓይነት መልስ ከፈለግህ ቅደሙንስ
        ለምን ጠየቅህ?››                               ‹‹ወንጌሉ እንደዛ አይልም ልጄ!፡፡››             ‹‹ልጄ እሷ ስለሆነችብህ አይደለም
                                                                                   የተጨነቅከው፡፡›› አሉት ባህታዊው፡፡
           ‹‹የኔ ጥያቄ ልሽሻት ወይስ መንገዴን ተሸክሜ           ‹‹አሁን ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም፡፡
        ልሂድ አይደለም፡፡››                         ከእሷ መለየቱን እፈራዋለሁ:: የኔ ብቻ እንዳልሆነች         ‹‹ነው እንጂ አባቴ፡፡ በጣም ነው የምወዳት፡፡››

                                                                                                       ወደ ገጽ  84  ዞሯል

        86                                                                                 “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ”                                                          ድንቅ   መጽሔት -  መስከረም  2012
   81   82   83   84   85   86   87   88   89   90   91