Page 5 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 5
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
ምስጋና
ለዚህ መጽሃፍ መጸነስ ዋነኛው መነሻ ከሐምሌ 2012 እስከ ጥቅምት 2013
በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ባወጧኋቸው ጽሁፎች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች ናቸው።
ስለዚህም፣ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጆችን እና አስተያየት የሰጡኝን ወገኖች ሁሉ
በቅድሚያ አመሰግናለሁ። ከዚህ በመቀጠል፣ የመጽሐፉን ረቂቅ በማንበብ ጠቃሚ
አስተያየት ለሰጡኝ ለአቶ በቀለ ባይሳ፣ አቶ ብርሐነ መዋ፣ ዶ/ር ጉልላት ከበደ፣ ዶ/ር
ሰለሞን አበበ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው እንግዳ፣ አቶ ማሞ ደስታ እና አቶ ሙሉጌታ አምሐ
ጥልቅ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እንዲሁም፣ በጋዜጣ የወጡትንም ሆነ የዚህን መጽሃፍ
ረቂቅ በማረም እና መጽሃፉ በተጻፈበት ወቅት አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛውን
አስተዋጽኦ ያበረከተችውን ባለቤቴን ወይዘሮ መቅደስ ቦጋለን፣ ክብረት ይስጥልኝ እላለሁ።
በመጨረሻም፣ የመጽሐፉን ሽፋን ያቀናበረውን እና ከመጽሐፉ ተደራሲያን ዋነኛው የሆነው
የወጣቱ ትውልድ አካል የሆነውን ልጄን አቶ ዳግማዊ ደስታ መብራቱን አመሰግናለሁ።
መታሰቢያነቱ
በአማርኛ የመጀመሪያዬ የሆነው ይህ መጽሃፍ፣
መልካምነትን፣ ዕውቀት መሻትን፣ ጥረትን፣ እና ጽናትን ላወረሱኝ ለአባቴ
ለአቶ መብራቱ በላይ እና ለእናቴ ለእማሆይ ፅጌ ማርያም (ዘነበች) በየነ
መታሰቢያ ይሁንልኝ።
v