Page 6 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 6
ደስታ መብራቱ
ለቅምሻ
የ1960ዎቹ ትውልድ እምነት እና ጽናት ዋነኛው ምንጭ በወቅቱ የነበረውን
ድህነት፣ ኋላቀርነት፣ ጭቆና እና አድልዎ ‘ለምን’ ብሎ መጠየቁ እና ሁኔታውን ለመቀየር
ቆርጦ መነሳቱ ነበር። ከዚህ ጋር ተያይዞ በየትኛውም ወገን ለተከፈለው መስዋአትነት ታላቅ
ክብር አለኝ። ገጽ 1
በምህዳራዊ አስተሳሰብ መሰረት አንድ ምህዳር ማለት የየራሳቸው ህልው
ነባራዊነት ያላቸው የተለያዩ ቁሳዊ ነገሮች እና ባህርያት (attributes) የተደራጁበት
የግንኙነት ስብስብ ነው። የምህዳራዊ ትንተናም ዋነኛው መለያው አንድን ውስብስብ
ምህዳር በጥቅልነቱ ለመረዳት የሚያስችሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን መጠየቁ ነው። ገጽ 17
ባሁኑ ሰዓት አብዛኛው የፖለቲካ ንግግሮቻችን (discourses) ከሚዛናዊነት
ይልቅ ስሜታዊነት፣ ከሩቅ አላሚነት ይልቅ ቅርብ አዳሪነት፣ ከአካታችነት ይልቅ አግላይነት
ጎልቶ ይታይባቸዋል። ይህም፣ ሃገሪቱን ከዕለት ወደ ዕለት ወደ ተባባሰ ቀውስ እየከታት
ይገኛል። ገጽ 22
ከሃገራዊው እውነታ ያልተጣጣሙ ጭፍን የአስተሳሰብ እመርታዎች፣ ለረጂም
ዘመናት ተንሰራፍቶ የኖረው ባላባታዊ የፖለቲካ ባህል ቅሪቶች፣ እና ውስብስብ ለሆነው
የሃገሪቱ የፖለቲካ ችግር የተቀነበቡ እና ቀላል የሆኑ (simplistic) መፍትሔዎች ለመሻት
እና ለማራመድ የተደረጉ ጥረቶች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ህመሞች ዋነኛ አእምሮአዊ
ምንጮች፤ ናቸው። ገጽ 23
የሃገረ መንግሥት ምስረታ ፈተናችን ዋነኛው አስኳል በሁለት ልዩ ታሪካዊ
ወቅቶች ከተራመዱ የአሃዳዊነት ሥርዓቶች ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ የማንነት ቀውሶች
(Identity crisis) ናቸው። ገጽ 45
የወንዳዊነት አስተሳሰብ ጎልቶ በሚታይበት የሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ ያለውን
ውስብስብ ችግር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የፖለቲካችንን ሴታዊነት ባህርይ
ማጠናከር ይኖርብናል። ገጽ 62
በምህዳራዊ አስተሳሰብ መሰረት፣ በማናቸውም ህብረተሰብ ውስጥ የሚገኙ
ተቃራኒ ተረኮችን ወደ ዐይነታዊ የለውጥ ተረክ ማምጣት ያንን ማህበረሰብ በዘላቂነት
ወደፊት ለማሻገር ቁልፍ እና አይነተኛ እርምጃ ነው። ገጽ 76
ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለፉት ሶስት የኢንዱስትሪ አብዮቶች በተሳታፊነት ሳይሆን
በበዪ ተመልካችነት አሳልፋለች። ከዚህ የበዪ ተመልካችነት እንድትወጣ ከተፈለገ፣
የሚወጡ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ የአራተኛውን የኢንዱስትሪ አብዮት ፈተናዎችን
በሚቀንስ እና እድሎቹን በሚያሰፋ መልኩ ሊቀረጹ እና ሊተገበሩ ይገባል። ገጽ 93