Page 11 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 11
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
ይህ መጽሐፍ እጅግ በጣም የሚያሳስበንን የወቅቱን የሃገራችንን ጉዳይ እስከአሁን
ድረስ ሲቀርቡ ከነበሩት ፖለቲካዊ አቀራረቦች ወጣ ባለ ሁኔታ አዲስ፣ ሁለንተናዊና ሳይንሳዊ
በሆነ የአመለካከት ስልት (ምሕዳራዊ አስተሳሰብ) ትንታኔ የሚያቀርብ ነው። በመጽሐፉ
የቀረቡት ትንታኔዎች የሃገራችንን የወቅቱን የፖለቲካ ቀውስ እና የኢኮኖሚ ችግሮች
ከምሕዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ በመተንተን የመፍትሔ አቅጣጫዎችንና ሊወሰዱ
የሚገባቸውን እርምጃዎች ያሳያሉ። የመፍትሔ አቅጣጫዎቹ የተሳሳቱ አመለካከቶችን
በአሳማኝና ሐቀኛ ምክንያቶች በመሞገትና ገንቢና አካታች የሆኑትን በማሳየት የቀረቡ
ስለሆኑ ብዙዎችን ሊያግባቡ ይችላሉ የሚል ዕምነት አለኝ። በመሆኑም ሁሉም የአገራችን
የፖለቲካ ተዋናዮችና መጪው ጊዜ የሚያሳስባቸው ወገኖች ሁሉ መጽሐፉን እንዲያነቡትና
ተገቢውን ትምህርት ወስደው ለሃገራችን የሰላምና የዴሞክራሲያዊ ሽግግር አስፈላጊ ለሆነው
ለብሔራዊ መግባባት ጥረት እንዲጠቀሙበት ለማሳሰብ እወዳለሁ። ፕ/ር ደስታ ይህን
ከቀውስ መውጫ አዲስ አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን አዲስ የአማርኛ ቃሎችን ጭምር ስለሰጡን
ሊመሰገኑ ይገባል።
አቶ በቀለ ባይሳ፣ የምክር ሥራ ባለሙያ፣ አዲስ አበባ
አገራችን በአንድ ገጹ እንደ መልካም ኣጋጣሚ በሌላው ደግሞ በስጋት የሚታይ
የለዉጥ ማዕበል ዉስጥ ባለችበት በአሁኑ ወቅት ፕሮፌሰር ዸስታ ይህን ወቅቱን የጠበቀ
መጽሃፍ ለኣንባቢው አበርክተዋል። መጽሃፉ ለየት ያለ ትንተናና ኣቀራረብ ያለዉና ላለንበት
ኣገራዊ ችግር ጠቃሚ የመፍታሔ ሃሳቦች ያዘለ ቢሆንም “…. ትንተናዎቹም ሆነ የመፍትሔ
ሃሳቦቹ ከአመላካችነት የዘለለ ድርሻ እንዳይሰጣቸው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፤
በመሆኑም በመጽሃፉ ዉስጥ የቀረቡትን ሃሳቦች ይበልጥ መፈተሽ እና ተለዋዋጭ ከሆነው
ሀገራው እና ዓለም ኣቀፋዊ እውነታ ጋር ኣዛምዶ መተንተን ከሁሉም ወገን የሚጠበቅ ድርሻ
ይሆናል” ይለናል ፕ/ር ደስታ በተለመደው ሙያዊ ትህትናው።
አቶ ሙሉጌታ አምሀ፣ ቪየና፣ ኦስትሪያ
3