Page 16 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 16

ደስታ መብራቱ


                  ለዚህም  እንዲረዳ፣  በያንዳንዱ  ክፍል  መዝጊያ  ላይ  የየክፍሉን  ቁልፍ  ሃሳቦች
           ባጭሩ ለማቅረብ ተሞክሯል። እነኚህን ቁልፍ ሃሳቦች በቅድሚያ ማንበብ፣ አንባቢዎች
           የመጽሃፉን  ዋነኛ  ጭብጦች  እንዲገነዘቡ  እና  ዝርዝር  ሃሳቦቹንም  በደንብ  ለመረዳት
           እንዲችሉ  ያግዛል  ተብሎ  ይታመናል።  በተጨማሪም፣  የመጽሀፉ  የመጀመሪያ  እትም
           ለፖለቲከኞቻችን እና ለወጣቱ ትውልድ ተደራሽነቱን ለሚያረጋግጡ ተቋማት፣ ሚዲያ እና
           የማህበረሰብ አንቂዎች በነጻ እንዲዳረስ ይደረጋል። በመጨረሻም፣ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ
           የተካተቱት  የምህዳራዊ  አስተሳሰብ  መርሆዎች  በማናቸውም  የህይወት  እና  ሙያ  ዘርፍ
           ተግባራዊ የሚደረጉ በመሆናቸው፣ አንባቢዎች እነኚህን መርሆዎች ለግልም ሆነ ለሙያ
           ህይወታቸው እንዲጠቀሙባቸው ይመከራሉ።
   11   12   13   14   15   16   17   18   19   20   21