Page 20 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 20
ደስታ መብራቱ
ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ባላፉት አስር ተከታታይ ዓመታት በመንግስትም ሆነ
በአንዳንድ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች እንዳመላከቱት ሃገራችን
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ከፍተኛ የሚባል የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች። በሌላ
1
በኩል ግን፣ የህዝቦች ሁለንተናዊ ደህንነት (wellbeing) ይበልጥ እያሽቆለቆለ እና የሃብት
ክፍፍል ክፍተቱም እየሰፋ መሄዱን የሚያመለክቱ በርካታ መረጃዎች አሉ። እንዲህ ዓይነቱ
የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ኢፍትሃዊነት በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ለሆነ ማህበራዊ ቀውስ እና
የህዝቦች ተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻ በመሆን ላይ ይገኛል። ካፒታል በሃያ አንደኛው ክፍለ
ዘመን የተሰኘውን ድንቅ የምርምር መጽሐፍ እ.አ.አ. በ2014 የጻፈው ኢኮኖሚስቱ ቶማስ
ፒኬቲ አበክሮ እንዳስገነዘበው፣ ባሁኑ ሰዓት የበላይነትን ይዞ የሚገኘው ሉላዊ
የካፒታሊስት ኢኮኖሚ ሥርዓት ለዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ዋነኛ መሰረት ከሆኑት
የማህበራዊ ፍትህ እሴቶች ጋር በእጅጉ የሚጋጭ በመሆኑ ሊታከም እንደሚገባው
ያመላክታል።
በአጠቃላይ፣ ባለፉት ጥቂት ዓስርተ ዓመታት ዓለማችን ከዚህ በፊት ታይቶ ወደ
ማይታወቅ ውስብስብ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ከባቢያዊ፣ እና ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ውስጥ
በመግባት ላይ ትገኛለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ በኢኮኖሚ
ሥርዓቱም ላይ ሆነ በዕለት ተዕለት ኑሮአችን ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማድረግ ላይ
የሚገኘው የመረጃ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታይዜሽንም ያለንበትን ሁኔታ ውስብስብነት ይበልጥ
እያጠናከረው እንደሚሄድ ይገመታል። እነኚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ቀውሶች
ተጠናክረው መውጣት ከጀመሩበት ከ1950ዎቹ ጀምሮ በተለያዩ የሳይንስ መስኮች ሰፊ
ጥናት ሲደረግባቸው ቆይቷል። ነገር ግን፣ የችግሮቹ ውስብስብነት በአንድ የሳይንስ ዘርፍ
የተቀነበበ ትንተና (reductionism) መረዳትም ሆነ መሰረታዊ መፍትሔ ማግኘት
እንዳይቻል አድርጎታል። የሳይንሱ ማህበረሰብ የእንዲህ ዓይነቱን አቀራረብ ውሱንነት
ይበልጥ እየተገነዘበ ሲመጣ፣ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የውሱንነቶቹን ዋነኛ ምንጮች ለመረዳት
እና ለፈተናዎቹ የሚመጥን ሳይንሳዊ ያተናተን ዘዴዎችን ወደማፈላለጉ አምርቷል። ይህም፣
የሳይንሳዊ አስተሳሰቦችን የፍልስፍና መሰረቶች እንደገና በጥልቀት እንዲመረምር
አስገድዶታል።
1 ሁለንተናዊ ደህንነት (wellbeing) የሰዎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አካባቢያዊ እና
ፖለቲካዊ ደህንነት በተቀናጀ ሁኔታ የሚዳስስ የልማት ፅንሰ-ሃሳብ ነው።