Page 25 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 25

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             ሳይንሶች ውስጥ  ውጤታማነታቸው  ዝቅተኛ ሊሆን  ችሏል።           ይህንን  የምሉዕነት  እና
                                                                          5
             ውስብስብነት  ዕውነታ፣  ካብዛኛዎቹ  ሳይንቲስቶች  በተሻለ  የሥነ  ጥበብ  ሰዎች
             እንደሚረዷቸው  እና  በሥራዎቻቸውም  ለማሳየት  እንደሚሞክሩ  የሚያሳዩ  መረጃዎች
             አሉ።

                     ከዚህ በታች ያለው ምስል አንድ፣ ከላይ የተጠቀሱት የምህዳራዊ ውስብስብነት
             ዓይነቶች በገሃዱ ዓለም ውስጥ ያላቸውን ድርሻ በስዕላዊ መግለጫ የሚያመላክት ነው።
             በዚሁ  መሰረት፣    የመጀመሪያው  ክፍል  እና  በገሃዱ  ዓለም  በጣም  አነስተኛውን  ድርሻ
             የሚወስደው የተደራጀ ቀላልነት በተቀነበበ ተንተና (reductionist analysis)  ሊጠና
             የሚችለውን  የቁሳዊውን ዓለም ይወክላል።        ይህም  ባብዛኛው  ፊዚክስ  እና  ኬሚስትሪ
             በመሰሉት የሳይንስ ዘርፍ የሚሸፈን ነው።
             ምስል 1፡ ምህዳራዊ ውስብስብነት





                          ያልተደራጀ ውስብስብነት (unorganized complexity)
                                                የተደራጀ ውስብስነት
              ብዝሃነት (diversity)             (Organized complexity)








                                የተደራጀ ቀላልነት
                             (Organized simplicity)




                                              ዘፈቀደነት (randomness)



             5  በእኔ እይታ ከሃገራችን የሥነ ጥበብ ሰዎች ታላቁ የሥነ ጽሁፍ ሰው ኦቦ ፀጋየ ገብረ መድህን፣
             ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ እና ገጣሚ ነቢይ መኮንን እዚህ ውስጥ የሚካተቱ ይመስለኛል።
                                                                        17
   20   21   22   23   24   25   26   27   28   29   30