Page 26 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 26

ደስታ መብራቱ


                  ከዚያ  ቀጥሎ  ያለው፣  በስታቲስትክሳዊ  ትንተና  (statistical  analysis)
           የሚሽፈነው እና  በበቂ ሁኔታ ተገማች ዘፈቀደነት (randomness) ያለው ያልተደራጀው
           ውስብስብነት (unorganized complexity) የዓለማችን ክፍል ነው። ለምሳሌም ያህል፣
           ያንድን ወረርሽኝ በሽታ ባህርይ እና የመሰራጨት አቅጣጫ ለማጥናት የሚካሄድ ጥናት
           በዚህኛው የዓለማችን ክስተት ውስጥ የሚካተት ይሆናል። አብዛኛው የዓለማችን ኩነት
           እና  ክስተት  ግን  የሚገኘው  የተደራጀ  ውስብስነት  (organized  complexity)  ተብሎ
           በሚታወቀው  ክፍል  ውስጥ  ሲሆን  ይህም  አብዛኛዎቹን  ማህበራዊ፣  ከባቢያዊ፣  እና
           ፖለቲካዊ  ምህዳሮች  ያካትታል።  እስካሁን  ድረስ  በአብዛኛው  እነኚህን  ምህዳሮች
           በተለመዱት የተቀነበበ እና ስታቲስቲካዊ ትንተና ለመረዳት እና ከእነርሱም ጋር የተያያዙ
           ችግሮችን    ለመፍታት  የተደረጉ  ጥረቶች  ችግሮቹን  ይበልጥ  እየተወሳሰቡ  እንዲሄዱ
           አድርገዋቸዋል። ስለሆነም ነው፣ በዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ምህዳሮችን ባግባቡ ለመረዳት
           የሚቻለው በምህዳራዊ ትንተና ብቻ ነው የሚባለው።

                  በምህዳራዊ  አስተሳሰብ  መሰረት  አንድ  ምህዳር  ማለት  የየራሳቸው  ህልው
           ነባራዊነት  ያሏቸው  የተለያዩ  ቁሳዊ  ነገሮች  እና  ባህርያት  (attributes)  የተደራጁበት
           የግንኙነት  ስብስብ  ነው።  የምህዳራዊ  ትንተናም  ዋነኛው  መለያው  አንድን  ውስብስብ
           ምህዳር በጥቅልነቱ ለመረዳት የሚያስችሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን መጠየቁ ነው። ከነዚህም
           ዋነኛው፣  በጊዜ  ሂደት  የሚከሰቱ  መሰረታዊ  መዋቅራዊ  ግንኙነቶች  (underlying
           structural relationships) እና የባህሪ ዘይቤዎች (patterns of behavior) ላይ የሚነሱ
           ጥያቄዎች ናቸው። በዚህ ላይ በመመርኮዝም፣ በምህዳሩ መስተጋብር ውስጥ ሊያጋጥሙ
           የሚችሉ  መዘግየቶች  (potential  delays)፣  አዎንታዊ  እና  አሉታዊ  ግብረመልሶች
           (positive and negative feedbacks) እና ያልተጠበቁ መዘዞቻቸው (consequences)
           ላይ ያተኩራል፡፡ ለዚህም እንዲረዳው፣ በተለያዩ የሳይንስ መስኮች በተለይም በተፈጥሮ
           የሳይንስ መስክ የተረጋገጡ አጠቃላይ ሳይንሳዊ መርሆዎችን በማቀናጀት ይጠቀማል።
   21   22   23   24   25   26   27   28   29   30   31