Page 22 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 22

ደስታ መብራቱ


           ተያይዞ ይህ ፉክክር ወደ አዲስ ደረጃ እየተሸጋገረ መጥቷል። የሁለገብ ዕውነት አመክንዮ፣
           በተለይም ከሃያኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ በፈጣን ሁኔታ ላደገው የመረጃ
           እና  ተግባቦት  (information  and  communication)  ቴክኖሎጂ  መሰረት  ለሆነው
                                                        3
           ተወራራሽ አመክንዮ (Fuzzy logic) መነሻ በመሆንም አገልግሏል ። ሳይንሳዊ እውቀታችን
           በከፊል እና ግራጫ እውነታዎች ላይ የተመሠረተ መሆኑን እውቅና መስጠቱ ውስብስብ
           እየሆኑ የመጡትን የዓለማችንን ስርዓቶች ለመረዳት እና ከዚህ ጋር ተያይዘው የመጡትን
           በርካታ ችግሮች መፍትሔ ለመሻት ቁልፍ እርምጃ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በባህሪያቸው እጅግ
           ውስብስብ  እየሆኑ  የመጡትን  ኢኮኖሚያዊ፣  ማህበራዊ  እና  አካባቢያዊ  ቀውሶችን
           ለመረዳት ለሚደረገው ጥረት ዋነኛ መሰረት ሊሆን ችሏል፡፡

                  በሌላ  በኩል፣  የምዕራባዊው  ሳይንስ  ዋነኛ  መለያ  የሆነው  የተቀነበበ  ትንተና
           ተፈጥሮን የራሱ ህልው የሂደት መርህ እንዳለው ፍጡር (organism) ሳይሆን እንደ አንድ
           ታላቅ  ማሺን  ሊጠና  እና  ጥቅም  ላይ  ሊውል  የሚችል  አካል  አድርጎ  ይወስዳል።  ይህ
           አመለካከት ለረጂም ጊዜ በሳይንሱም ሆነ በጠቅላላው ዘመናዊ አስተሳሰብ ውስጥ ታላቅ
           ተጽእኖ ያለው የአመለካከት ዘይቤ (metaphor) ሆኖ ዘልቋል፡፡ ይህ አቀራረብ፣ በተለይ
           በተፈጥሮ  ሳይንስ  መስክ  ለተገኘው  ሰፊ  የዕውቀት  ጥልቀት  ከፍተኛውን  አስተዋጽኦ
           አድርጓል፤ ወደፊትም እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በሌላ በኩል ግን፣ ከሃያኛው ክፍለዘመን
           መጀመሪያ አንስቶ አንድ ተገዳዳሪ የሆነ የተፈጥሮ ምህዳርን በማያቋርጥ፣ ተለዋዋጭ እና
           ተወራራሽ መስተጋብራዊ ምሉዕነቱ የሚመለከት ንዑስ የሳይንሳዊ አመለካከት ዘርፍ ብቅ
           ማለት ጀመረ። ይህ አመለካከት፣ ከአንድ ወጥ እና ብቸኛ         (deterministic)  አካሄድ
           ይልቅ የማያቋርጥ ፈጠራን፣ ከቁስ ይልቅ ሂደትን፣ ከክፋዮች ይልቅ ምሉዖችን ያጎላል፡፡
           የሰውን  እና  የተፈጥሮ  ንፍቀ  ክበብን  አንድ  ላይ  ከማገናኘቱም  በላይ  ገሃዱን  ዓለም
           እንደማያቋርጥ የኃይል እና የቁስ ፍሰት መስተጋብር አድርጎ ያሳያል። በዚህም ሁለንተናዊ
           እይታ (holistic view) ተብሎ ለሚጠራው መሠረት ጥሏል፡፡

                  በሁለንተናዊ አስተሳሰብ (holistic thinking) መሠረት፣ ማናቸውም ምሉእነት
           ያለው ቁስ ሆነ ሕይወት የተመሰረተው የራሳቸው ምሉዕነት ባላቸው ክፋዮች ቅንጅታዊ
           አደረጃጀት ነው።  የሁለንተናዊው አመለካከት ቀዳሚው አቀንቃኝ የነበረው ጃን ስሙትስ
           (Jan Smuts) እንዳለው የ 'ምሉዕነት' ባሕርይ በሁሉም ቦታ የምናገኘው እና በአጽናፈ
           ሰማይ (universe) ውስጥ ለሚታየው ማንኛቸውም ተፈጥሯዊ ዝግመተ ለውጥ መነሻ
           ነው።  ስለዚህም፣ ምሉእዎች ሰው ሰራሽ የአስተሳሰብ ግንባታዎች ሳይሆኑ በአጽናፈ-ሰማይ
           ውስጥ  የሚገኘውን  እውን  ነገር  ያመለክታሉ።  ለምሳሌም፣  አንድን  እጽ  ወይም  እንስሳ
           ብንወስድ፣ የዚህ  እጽ ወይም እንስሳ ምሉዕ ባህርይ ከክፋዮቹ ተደማሪነት ባሻገር በክፋዮቹ
           መካከል  ባለው  መስተጋብራዊ  ግንኙነት  የሚወሰን  ይሆናል።  በዚያው  መጠን  ደግሞ፣


           3  አንዳንድ ጥናቶች፣ የቻይና እና የህንድ ባለሙያዎች በኮምፕዩተር ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ
           ያላቸውን የበላይነት ከዚሁ በምሥራቁ ዓለም በሰፊው ካለው የሁለገብ ዕውነት አመክንዮ ቅኝት
           ጋር ያያይዙታል።
   17   18   19   20   21   22   23   24   25   26   27