Page 27 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 27

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             1.5 ምህዳራዊ አስተሳሰብ እና ሃገር በቀል ዕውቀት

                     በተለያዩ  ጥናቶች  እንደተረጋገጠው፣  ህጻናት  አብዛኛውን  የገሃዱን  ዓለም
             የመጀመሪያ  ዕውቀቶቻቸውን  የሚያዳብሩት  በቅድሚያ  የምሉዕ  ምህዳሩን  ስሜት
             ተወራራሽ  በሆነ  አመክንዮ  (transductive  logic)  በመገንዘብ  ነው።  ይህ  ባብዛኛው
             ህጻናቶች  ላይ  የሚታይ  አመክንዮ፣  ከአጠቃላይ  ወደ  ተናጠል  (deductive)  ወይንም
             ከተናጠል  ወደ  አጠቃላይ  (inductive)  ከሚሄደው  አመክንዮ  በተለየ  አንድን  ተናጠል
             ሁኔታ ከሌላ ተናጠል ሁኔታ ጋር በቀጥታ የሚያገናኙበት መንገድ ነው። ይህም፣ ሁሉም
             የሰው ፍጡር የሁለንተናዊ አስተሳሰብ ክህሎት በተፈጥሮ የተሰጠው መሆኑን ያሳያል።
             እንዳለመታደል ሆኖ፣ አብዛኛዎቻችን በተቀነበበ ትንተና ላይ በተመረኮዘው የምዕራባዊያን
             የትምህርት  ሥርዓት  ሳጥን  ውስጥ  ባለፍንበት  መጠን  ይህንን  ተፈጥሮአዊ  የሁለንተናዊ
             አስተሳሰብ ክህሎታችንን እያቀጨጭነው እና እያጠፋነው እንሄዳለን። ከዚህም የተነሳ፣
             በተለምዶ እንደሚባለው እና በተግባርም እንደሚታየው፣ ባንድ የሳይንስ ዘርፍ በጣም
             ጥልቅ የሆነ ዕውቀት ባለቤት የሆነ ሳይንቲስት፣ በአብዛኛው ከዚያ የሙያ ዘርፍ ውጭ ባሉ
             ዘርፎች ከፍተኛ ለሆነ የዕውቀት ድህነት የተጋለጠ ይሆናል።

                     ከዚህ በተቃራኒው፣  ለምንም ዓይነት ዘመናዊ ትምህርት ሳይጋለጡ በተፈጥሮ
             የተሰጣቸውን የሁለንተናዊ አስተሳስብ ክህሎት በህይወት ልምዶቻቸው በማዳበር እጅግ
             ከፍተኛ የሆነ አስተዋይነታቸውን ያስመሰከሩ የማህበረሰብ አዋቂዎች በሁሉም የህብረተሰብ
             ታሪክ ውስጥ እንደነበሩ እና አሁንም እንዳሉ ይታወቃል። እነኚህ የማህበረሰብ አዋቂዎች፣
             ሃገራችንን  ጨምሮ፣  ለበርካታ  የዓለማችን  ማህበረሰቦች  ለዘመናት  አብሮ  የመኖር  እና
             ከተፈጥሮ አካባቢያቸውም ጋር በሚዛናዊነት ለመዝለቅ ዋነኛ የዕውቀት መሰረቶች በመሆን
             አገልግለዋል።  ሃገር  በቀል  ዕውቀት  በመባል  የሚታወቀው  የዕውቀት  ዘርፍ  እነኚህ
             የማህበረሰብ አዋቂዎች ያመነጯቸው እና በዘመናት ሂደት ውስጥ በማህበራዊ ይሁንታ እና
             ቅብብሎሽ እየዳበረ ለመጣው የዕውቀት ዘርፍ ዋነኛ ማከማቻ (repository) ነው።

                     እዚህ ላይ፣ በሀገር በቀል እውቀቶች እና በማህበራዊ ልማዶች መካከል ያለውን
             የይዘት  ልዩነት  መረዳት  ተገቢ  ይሆናል።  በርካታ  ሰዎች፣  በአንዳንድ  ሁኔታ  ጎጂ  የሆኑ
             ማህበራዊ  ልማዶችን (rituals) በዘመናት ሂደት ከዳበሩ አና  የማህበራዊ እሴቶች ቋት
             ከሆኑት  ሃገር  በቀል  እውቀቶች  ጋር  በማምታታት  የዚህን  የዕውቀት  ዘርፍ  አስተዋጽኦ
             ሲያጣጥሉ  ይሰማል።  የዚህ  ዕውቀት  ዘርፍ  ዋነኛው  የትንተና  መሰረቱ  ተፈጥሮአዊው
             የሁለንተናዊ አመለካከት ክህሎት በመሆኑ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ በሃያኛው ክፍለ
             ዘመን  ውስጥ  እየዳበረ  ከመጣው  ምህዳራዊ  ሳይንስ  ጋር  በአብዛኛው  የተጣጣመ  ሆኖ
             ይገኛል። ለምሳሌም ያህል፣ በምህዳራዊ አስተሳሰብ መሰረት፣ መተካካት (succession)
             የማናቸውም ምህዳር ዘላቂነት ዋነኛው ማረጋገጫ መርህ ነው። በመሆኑም፣ በማናቸውም
             ተፈጥሮአዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ምህዳሮች ላይ ይሰራል።



                                                                        19
   22   23   24   25   26   27   28   29   30   31   32