Page 23 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 23

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             ይኸው ምሉዕ እጽ ወይም እንስሳ ከአካባቢው ጋር የሚኖረው መስተጋብራዊ ግንኙነት
             በውስጡ ያሉት ክፋዮች የሚኖራቸውን የቅርጽ እና የተግባር ባህርይ ይወስናል።

                     በዚህ  መልኩ፣  በምሉዕ  እና  በክፋዮች  መካከል  የሚከናወነው  የማያቋርጥ
             መስተጋብር  የአጠቃላዩ  አጽናፈ-ሰማይ  መሰረት  በመሆን  ያገለግላል።  በሁለንተናዊ
             አስተሳሰብ መሰረት፣ የተቀነበበ ትንተና (reductionist analysis) ባጠቃላዩ የሁለንተናዊ
             እይታ ማዕቀፍ ውስጥ ስለ አንድ ውስን ክፋይ ጠለቅ ያለ ዕውቀት ለማመንጨት የራሱ
             ጠቀሜታ እንዳለው ይገነዘባል። ውስብስብ የሆኑ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ እና ከባቢያዊ
             ምህዳሮችን ባግባቡ ለመረዳት ግን ይህ አመለካከት በሁለንተናዊ አስተሳሰብ መቃኘት
             ይኖርበታል።



























                                                                        15
   18   19   20   21   22   23   24   25   26   27   28