Page 24 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 24
ደስታ መብራቱ
1.4 የምህዳራዊ አስተሳሰብ መሰረቶች
ምህዳራዊ አስተሳሰብ (Systems thinking) ከዚህ በላይ በተጠቀሱት አማራጭ
የፍልስፍና እና የዓለም እይታ (world view) ላይ በመመስረት ከ1960ዎቹ ጀምሮ እየዳበረ
የመጣ የሳይንስ መስክ ነው። መነሻ ነጥቡም፣ በተቀነበበ ትንተና ላይ የተመረኮዘው
ምዕራባዊው ሳይንስ ለሰው ልጆች ህይወት መሻሻል ያደረገውን እና ወደፊትም ሊያደርግ
የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተገንዝቦ ለድክመቶቹ ምንጭ የሆኑትን የፍልስፍና እና
የአተናተን መሰረቶች መመርመር እና መፈተሽ ነው። በዚህም፣ ከተለያዩ የሳይንስ መስኮች
የተገኙትን ዕውቀቶች በተለየ የዕውቀት አደረጃጀት በማስተሳሰር ጎጂ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ
ተጽእኖዎቻቸውን (second-degree effect) ለመቀነስ የሚያስችል ሁኔታን ሊፈጥር
ችሏል። ለዚህም የሚጠቀምበት የአጠናን ዘዴ የልዕለ-ዘርፍ (transdisciplinary) የአጠናን
4
ዘዴ ተብሎ ይታወቃል። በዚህ ሂደትም የተነሳ፣ ባለፉት ጥቂት ዓስርተ ዓመታት፣
ምህዳራዊ አስተሳሰብ በተለያዩ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ መስኮች የየራሱን ልዩ
ገጽታ በመያዝ በመተግበር ላይ ይገኛል። ከዚህም ውስጥ አንደኛው ምሳሌ፣ አምስተኛው
ዘርፍ (The fifth discipline) ተብሎ የሚጠቀሰው እና በድርጅታዊ ሥራ አመራር ዘርፍ
ሰፊ ተቀባይነት ያገኘው የምህዳራዊ አስተሳሰብ ትግበራ ነው።
የዘመናዊው ሳይንስ ዋንኛው መሰረት የሆነው የእንቅስቃሴ ሳይንስ
(mechanics) የተወሰኑ አይነት ግንኙነቶች ከሌሎች የበለጠ አስፈላጊ እንደሆኑ በመገመት
ውስብስብ ምህዳሮችን ወደ ቀላል ክፍልፋዮች በመቀነስ ላይ በመመርኮዝ የሚከናወን
የጥናት ሥርዓት ነው፡፡ ይህም፣ በተደራጀ ቀላልነት (organized simplicity) ላይ
የተመረኮዙ መፍትሔዎችን ይሰጣል። የዚሁ ተቀጽላ የሆነው በስታቲስቲክሳዊ ዘፈቀዳዊነት
(statistical randomness) ላይ የተመረኮዘው አተናተን፣ አንድ ምህዳር ውስብስብ
ቢሆንም በበቂ ሁኔታ ተገማች የሆነ ዘፈቀዳዊነት እስካለው ድረስ በስታቲስቲክሳዊ የአጠናን
ዘዴ ሊተነተን ይችላል ይላል። ይህም፣ በዓለማችን ለሚገኙ በጣም ጥቂት ለሆኑ
ያልተደራጀ ውስብስብነት (unorganized complexity) ላላቸው ክስተቶች የሚሰራበት
ሁኔታ እንዲኖር አስችሏል።
ነገር ግን፣ አብዛኛው ገሃዱ ዓለም፣ የተደራጀ ውስብስነት (organized
complexity) ባላቸው ምህዳሮች የተሞላ በመሆኑ በተደራጀ ቀላልነት ላይም ሆነ
ባልተደራጀ ውስብስብነት ላይ የተመረኮዙ መፍትሔዎች በሙሉ ጊዜያዊ (tentative) እና
ያልተሟሉ ይሆናሉ። ከላይ የተጠቀሰው የተቀነበበ ትንተና፣ እንደ ሂሳብ፣ ፊዚክስ፣ እና
ኬሚስትሪ በመሳሰሉ የሳይንስ መስኮች አንጻራዊ ውጤታማነት ያሳየ ሲሆን ውስብስብነት
ጥልቅ ተፈጥሮአዊ (inherent) ባህሪያቸው ለሆኑት እንደ ሥነሕይወት እና ማህበራዊ
4 ይህ ዓይነቱ የአጠናን ዘዴ በተለይ በምህንድስናው ዘርፍ አስቀድሞ የተተገበረ እና ከፍተኛ
ውጤትም ያስገኘ ነው። ለምሳሌም ያህል ባለፉት ጥቂት ዓስርተ ዓመታት ከፍተኛ ውጤት
ያስመዘገቡትን የዘረ መልዕ ምህንድስና (Genetic engineering)፣ የሥነህይወት ቴክኖሎጂ (Bio
technology) እና የናኖ ቴክኖሎጂን (Nano Technology) መጥቀስ ይቻላል።