Page 29 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 29
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
ሃገራት በሚገኙ ማህበረሰቦች በስፋት የሚተገበረው የኡቡንቱ (Ubuntu) ጽንስ ሃሳብ
አንደኛው ነው።
የኡቡንቱ አስተሳሰብ በጥቅሉ ‘እኔ እኔን የሆንኩት ባንተ እና በእናንተ ነው’
ይላል። ይህ አባባል የአንዱ ህልውና በሁሉም ላይ እና የሁሉም ዘላቂነት ደግሞ ባንዱ ላይ
ያለውን የህልውና ተደጋጋፊነት (interdependence) ያመላክታል። ኡካማ (Ukama)
የሚባለው አስተሳሰብ ሌላው ከዚሁ ጋር የተያያዘ ጽንስ ሃሳብ ሲሆን ይህ አስተሳሰብ
በቀደመው ፣ በአሁኑ እና በመጪው ትውልድ መካከል የማይነጣጠል አንድነትን ያቀፈ
ከመሆኑም በላይ የሰው ልጅ ከተፈጥሮአዊው (biophysical)) ዓለም ጋር ያለውን ቁርኝት
ያሰምርበታል። እነኚህ ሁለት አስተሳሰቦች፣ ከሁለንተናዊው አስተሳሰብ ጋር በቅርብ
የተዛመዱ ከመሆናቸም በላይ በሰው እና የተፈጥሮ አካባቢ ሁለንተናዊ ደህንነት
(Wellbeing) መካከል ያለውን ጥብቅ ትስስር ያሳያሉ። በአጠቃላይ፣ በዘመናዊው ሳይንስ
እና ሃገር በቀል ዕውቀቶች መካከል የሚፈጠር ስልታዊ ቅንጅት ዛሬ ለተጋፈጥናቸው
በርካታ ውስብስብ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማመንጨት ጠቃሚ አስተዋጽኦ ሊያደርግ
እንደሚያስችል ይታመናል።
የክፍል አንድ ቁልፍ ሐሳቦች
i. የተፈጥሮ አካባቢያችን፣ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳዊ ግብዓቶችን ከመስጠት
ባሻገር የዕውቀቶቻችን ሁሉ ዋነኛ ምንጭ በመሆን አገልግሏል። በመሆኑም፣
ከዝቅተኛው የቴክኖሎጂ ውጤቶቻችን እስከ ከፍተኛው የዘመናችን ሰው-ሰራሽ
ብልህነት (arficial intelligence) ድረስ ያሉ የቴክኖሎጂ ዕውቀቶች በሙሉ
ተፈጥሮን በማጥናት እና በማስመሰል (mimcry) ላይ የተመረኮዙ ናቸው።
ii. ከሃያኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ የታየው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት
በምድራችን የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት ላይ ያስከተለው ተጽእኖ መጠነ ሰፊ
በመሆኑ እና ከምድራችን የማዋሃድ አቅም በላይ በመሆኑ ዓለም አቀፋዊ ይዘት
ያለው ፈተና ደቅኗል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ሃገሮች፣ በተለይም በማደግ ላይ
ያሉ ሃገሮች፣ በኢኮኖሚያቸው ላይ ያላቸውን ሉዓላዊነት የሚያሳጣው ሉላዊነት
(globalization) ባራመዳቸው የተዛቡ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች የተነሳ ባለፉት
ሃምሳ እና ስልሳ ዓመታት ውስጥ በሃገሮች ውስጥ እና በሃገሮች መካከል ከፍተኛ
የሃብት ልዩነት በመፍጠር ዕልፍ ዓዕላፋትን ለከፋ ድህነት እና የኑሮ ጉስቁልና
ዳርጓል።
iii. በዚህም የተነሳ፣ ዓለማችንን ወይ ሊያጠፋት ወይንም በመሰረታዊነት ሊቀይራት
ወደሚችል ፍጹም የሰው ልጅ ጭፍን የበላይነት ዘመን (the Anthopocene
age) እንደገባን የሚያሳዩ በርካታ ሳይንሳዊ መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ።
ይህ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ፣ የዓለማችን ከባቢያዊ ሁኔታ መዛባት ብቻ ሳይሆን
የሰው ልጅም እንደፍጡር መቀጠል (existential) ፈተና ውስጥ ሊገባ
እንደሚችል ይገመታል።
21