Page 33 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 33

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     የዚህ ተምሳሌታዊ ምስል ዋነኛው ትኩረት ከምህዳራዊ አስተሳስብ አኳያ አንድን
             የፖለቲካ ምህዳር የመተንተኛ መንገድ ለማሳየት ነው።


                                       ሁነቶች
                                      (Events)        ስሜታዊ ምላሽ
                 በግላጭ የሚታይ                              Reactive
                   (Visible)           ሂደቶች
                                     (Patterns)


                                      መዋቅሮች
                  የማይታየው             (Structure)       ፋና-ወጊ ምላሽ
                  (Invisible)                           (Proactive)

                                  አእምሮአዊ ምንጮች
                                  (Mental models)


             ምስል 2፡ የፖለቲካ ምህዳር የበረዶ ቋጥኝ (Iceburg)

                     አንድን የፖለቲካ ምህዳር በምህዳራዊ ትንተና መነጽር ስንመለከት አራት አበይት
             ክፍሎች እናገኛለን። የመጀመሪያው ከማንኛውም ሰው የዕለት ተዕለት ህይወት ጋር በቀጥታ
             ወይንም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የተያያዙ እና በቀላሉ ሊታዩ የሚችሉ ማህበራዊ እና
             ፖለቲካዊ ሁነቶች ናቸው። ባንድ ወቅት እና አካባቢ የሚከሰት የተፈጥሮ ድርቅ፣ የኑሮ
             ወድነት፣  የወንጀል  መስፋፋት፣  እና  የፀጥታ  መደፍረስ  ለዚህ  ምሳሌ  ሊሆኑ  ይችላሉ።
             በአንድ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሁነቶች በተደጋጋሚ በሚከሰቱበት ወቅት
             ጥልቅ የሆነ የአመለካክት እና መዋቅራዊ ህመምን የሚያመላክቱ ሂደቶችን ይፈጥራሉ።
             ሁነቶችም ሆኑ ሂደቶች በአብዛኛው በግልጽ የሚታዩ እና ለስሜታዊ ምላሽ የሚያነሳሱ
             ናቸው።  ያንድን የፖለቲካ ምህዳር መስረታዊ  ህመሞች ለመረዳት  ግን ሥልታዊ በሆነ
             መንገድ የሁነቶችን እና ሂደቶችን ጤናማነት ወይንም ታማሚነት የሚወስኑትን እና ጥልቀት
             ያላቸውን መዋቅራዊ እና ያስተሳሰብ ምንጮችን መመርመር ያሻል።

                     ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሃገራችን ገንነው የሚታዩ የፖለቲካ ውይይቶች እና
             መጣጥፎች በአብዛኛው የሚያተኩሩት የተናጠል ሁነቶችን እና ሂደቶችን በመተንተን እና
             የግልም ሆነ የድርጅት አቋምን ማንጸባረቅ ላይ ሆነው ይታያሉ። ይህም በመሆኑ፣ ባሁኑ
             ሰዓት አብዛኛው የፖለቲካ ንግግሮቻችን (discourses) ከሚዛናዊነት ይልቅ ስሜታዊነት፣
             ከሩቅ  አላሚነት  ይልቅ  ቅርብ  አዳሪነት፣  ከአካታችነት  ይልቅ  አግላይነት  ጎልቶ
             ይታይባቸዋል።  ይህም፣  ሃገሪቱን  ከዕለት  ወደ  ዕለት  ወደ  ተባባሰ  ቀውስ  እየከተታት
             ይገኛል።
                                                                        25
   28   29   30   31   32   33   34   35   36   37   38