Page 31 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 31

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     ሳይጋለጡ በተፈጥሮ የተሰጣቸውን የሁለንተናዊ አስተሳስብ ክህሎት በህይወት
                     ልምዶቻቸው  በማዳበር  እጅግ  ከፍተኛ  የሆነ  አስተዋይነታቸውን  ያስመሰከሩ
                     የማህበረሰብ  አዋቂዎች  በሁሉም  የህብረተሰብ  ታሪክ  ውስጥ  እንደነበሩ  እና
                     አሁንም እንዳሉ ይታወቃል።
                x.   ሃገር በቀል ዕውቀት በመባል የሚታወቀው የዕውቀት ዘርፍ እነኚህ የማህበረሰብ
                     አዋቂዎች ያመነጯቸው እና በዘመናት ሂደት ውስጥ በማህበራዊ ይሁንታ እና
                     ቅብብሎሽ  እየዳበረ  ለመጣው  የዕውቀት  ዘርፍ  ዋነኛ  ማከማቻዎች
                     (repositories)  ናቸው።  የዚህ  ዕውቀት  ዘርፍ  ዋነኛው  የትንተና  መሰረቱ
                     ተፈጥሮአዊው የሁለንተናዊ አመለካከት ክህሎት በመሆኑ በጣም በሚያስገርም
                     ሁኔታ በሃያኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ እየዳበረ ከመጣው ምህዳራዊ ሳይንስ ጋር
                     በአብዛኛው የተጣጣመ ሆኖ ይገኛል።
               xi.   ባለፉት  ጥቂት  ዓስርተ  ዓመታት  በዓለማችን  ዙሪያ  እየተጠናከረ  ከመጣው
                     ተደራራቢ  ቀውሶች  እና  ከምህዳራዊ  አስተሳሰብ  እየበለጸገ  መምጣት  ጋር
                     በተያያዘ  ለሃገር  በቀል  ዕውቀቶች  የሚሰጠው  እውቅና  ይበልጥ  እየተጠናከረ
                     በመምጣት ላይ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ በዘመናዊው ሳይንስ እና ሃገር
                     በቀል  ዕውቀቶች  መካከል  የሚፈጠር  ስልታዊ  ቅንጅት  ዛሬ  ለተጋፈጥናቸው
                     በርካታ  ውስብስብ  ችግሮች  ዛላቂ  መፍትሔ  ለማመንጨት  እንደሚያስችል
                     ይታመናል።




















                                                                        23
   26   27   28   29   30   31   32   33   34   35   36