Page 35 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 35

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     ይህ  ህመም  በአሁኑ  ወቅትም  አብዛኛዎቹ  የሃገራችን  የፖለቲካ  ድርጅቶች
             በሚያራምዷቸው የፖለቲካ ፕሮግራሞች እና ፖሊሲዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሲያሳድር
             ይስተዋላል። ከተለያዩ ሃገሮች ማህበረሳባዊ ተመክሮ እና የእውቀት ክምችት መማር እና
             ጠቃሚውን  መርጦ  መውሰድ  አስፈላጊ  መሆኑ  አጠራጣሪ  አይደለም።  ነገር  ግን  ይህንን
             እውቀት ከሃገራዊው እውነታ እና የእውቀት መሰረት ጋር ማጣጣም እና ማዋደድ ዘላቂ እና
             አስተማማኝ የሆነ እድገት ለማምጣት እጅግ በጣም ወሳኝነት ያለው መሆኑን ባለፉት ሰባ
                                                              11
             ዓመታት ከፍተኛ እድገት ካስመዘገቡ ሃገራት ልምድ መረዳት ይቻላል ። ከዚህ  የጭፍን
             እመርታ  ህመም  መላቀቃችን  የሃገራችን  ፖለቲካም  ሆነ  የኢኮኖሚ  እድገት  መስመርን
             ለማቃናት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።

                     ባላባታዊ  የፖለቲካ  ቅሪቶች፡  ዘመናዊው  ፖለቲካ  ምናልባትም  ካንድ  ምዕተ
             ዓመት ያልዘለለ እድሜ ያለው ቢሆንም፣ ሃገሪቱ ካላት የረጅም ዘመን ታሪክ ጋር በተያያዘ
             ስር የሰደዱ ከባቢያዊ የፖለቲካ ባህሎች እንዳሏት አይካድም። ከነዚህም ውስጥ፣ ለሃገሪቱ
             የወደፊት እድገት ጠቃሚ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ በርካታ አስተዳደራዊ ሥርዓቶች
             እና ልማዶች የመኖራቸውን ያክል ለዘመናት ተንሰራፍቶ የኖረ ባላባታዊ የፖሊቲካ ባህልም
             ነበረ፡፡ የሚያሳዝነው ነገር፣ የዘመናዊው ፖለቲካ አራማጅ ሆኖ የተነሳው የ1960ዎቹ (የእኔ)
             ትውልድ  በሃገሪቱ  ከነበሩት  የዘመናት  ሃገራዊ  የአስተዳደር  እና  የፖለቲካ  ልምዶች
             ጠቃሚውን ከመውሰድ ይልቅ በሚያስገርም ደረጃ የባላባታዊው የፖለቲካ ባህል እስረኛ
             መሆኑ ነው። ይህም በመሆኑ፣ አብዛኞቹ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅቶች በተሟላ ነፃነት ላይ
             ከተመረኮዘ  ፖለቲካዊ  አካሄድ  ይልቅ  ፖለቲካዊ  ጭሰኝነትን  (political  serfdom)
             የሚያራምድ የፖለቲካ ሂደት ሲተገብሩ ኖረዋል።

                     እስከ  ዛሬም  ድረስ  በፖለቲካችን  ውስጥ  ስር  ሰዶ  የሚታየው  የመጠፋፋት
             ፖለቲካ የዚሁ ባላባታዊ ፖለቲካ ቅሪት ውጤት መሆኑ አያጠያይቅም።  ባለፉት ሃምሳ እና
             ስልሳ ዓመታት ውስጥ እንዲህ አይነቱን ፖለቲካዊ ጭሰኝነት አንቀበልም ብለው የተነሱ
             በርካታ ወጣቶች በየራሳቸው ድርጅቶች መቀጠፋቸውም የፖለቲካችን አንዱ አሳዛኝ ገጽታ
             ነው ። በአሁኑ ወቅት ከዚህ ባላባታዊ የፖለቲካ ቅሪት ነፃ የሆኑ ወጣት ፖለቲከኞች እና
                12
             የህብረተሰብ መሪዎች በአንዳንድ ድርጅቶች አካባቢ ብቅ ያሉ ቢሆንም በተመሳሳይ ፈተና
             እንዳይጠለፉ ከፍተኛ ስጋት አለ። ስለሆነም፣ ሁሉም የፖለቲካ እና የማህበረሰብ መሪዎች
             በተለይም ወጣት ፖለቲከኞቻችን ከእንደዚህ ዓይነቱ በሽታ ራሳቸውን ለማንጻት መጣር
             ይኖርባቸዋል።





             11  በዚህ ረገድ፣ ጃፓን እና ቻይናን ጨምሮ ክ1950ዎቹ ወዲህ ከፍተኛ እድገት ያስመዘገቡት የሩቅ
             ምስራቅ ሃገሮች ይጠቀሳሉ።
             12  ይህ ጉዳይ፣ አብዛኞቹ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሁነኛ ስፍራ የነበራቸው
             ድርጅቶች ንስሃ ሊገቡበት የሚገባ ነው።
                                                                        27
   30   31   32   33   34   35   36   37   38   39   40