Page 39 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 39

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ




                        ትብብር እና ፉክክር፡  በዚህ  መርህ  መሰረት፣  የማንኛውም  ምህዳር
             ውጤታማነት እና ዘላቂነት የሚወሰነው በክፋዮቹ መካከል ለሚኖረው ትብብር እና ፉክክር
             በሚኖረው አያያዝ ውጤታማነት ይሆናል። በክፋዮቹ አካላት መካከል የሚኖረው ትብብር
             የምህዳሩን አሰራር ውጤታማነት እና መረጋጋት (efficiency and stability) የሚወስን
             መሰረታዊ ጉዳይ ሲሆን በነኚሁ ክፋዮች መካከል የሚኖረው ፉክክር እና ውድድር ደግሞ
             ለምህዳሩ ቀጣይ እድገት አስፈላጊ ለሆነው ፈጠራ (innovation) ዋነኛ መሰረት ነው።

                     በዚህ መሰረት፣ በአንድ ሃገር ውስጥ የሚኖረው  የፖለቲካ  ምህዳር  ጤናማነት
             የሚወሰነው  በፓርቲዎች  መካከል  ሊኖር  በሚገባው  የመተባበሪያ  ማእቀፍ  ጥንካሬ  እና
             በመወዳደሪያ  ሜዳው  አካታችነት  ይሆናል።  የአንድ  ሃገር  ህገመንግስት  የፓርቲዎችን
             የመተባበሪያ  ማዕቀፍ  የሚወስን  ዋነኛ  መሰረት  ሲሆን  በማናቸውም  ሁኔታ  ዘላለማዊ
             ምሉዕነት ሊኖረው አይችልም። በመሆኑም በሁሉም ወገኖች ተሳትፎ እና ቅቡልነት ባለው
             አካሄድ በቀጣይነት መዳበር ይኖርበታል። ይህንን ሂደት በመወዳደሪያነት ለህዝብ ድምጽ
             መቅረብ ከሚገባቸው የፓርቲ ፕሮግራሞች እና ፖሊሲዎች መለየትም እጅግ በጣም አስፈላጊ
             ነው።  የሃገራችን  የፖለቲካ  ምስቅልቅል  አንደኛው  ምንጭ  ይህንን  ሃገራዊ  የመተባበሪያ
             ማዕቀፍ ከፓርቲዎች የመወዳደርያ ፕሮግራም ጋር ከማደበላለቅ የሚመነጭ ነው።

                     መዘርዝራዊ እና መስተጋብራዊ ውስብስብነት፡ በዚህ መርህ መሰረት፣  በአንድ
             ምህዳር  ውስጥ  ባለ  መዘርዝራዊ  (detailed)  እና  በመስተጋብራዊ  (dynamic)
             ውስብስብነት መካከል ሊኖር የሚችለውን ግንኙነት እና ልዩነት መረዳት አስፈላጊ መሆኑን
             ያመለክታል። ይህም ማለት፣ ለአንድ ውስብስብ ሁኔታ ሁለንተናዊ መፍትሔ ለማግኘት
             ከተናጠል ሁነቶች (events) እና ድግግሞሽ (patterns) ባሻገር በመመልከት መዋቅራዊ
             ምንጮችን  በጥልቀት  መመርመር  እና  መፍታት  የግድ  ይላል።  በተናጠል  ሁነቶች  ላይ
             ተመርኩዞ ሃገራዊ መፍትሔ ለመሻት የሚደረጉ ጥረቶች መውጫ ወደሌለው መዘርዝራዊ
             ውስብስብነት ይከታል። ከዚህ ይልቅ፣ የአመለካከት እና መዋቅራዊ ችግሮችን በመመርመር
             በርካታ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ ልዩ ቋጠሮዎችን (dynamic knots) መፍታት
             ይቻላል።
                     በዚህ  ሂደት  ውስጥ፣  አንድን  ውስብስብ  ሁኔታ  ለመፍታት  ካንድ  በላይ
             የመፍትሔ መንገዶች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገንዘብ ይገባል። እስከአሁን ድረስ ለኢትዮጵያ
             የፖለቲካ ችግሮች የሚጠቆሙ መፍትሄዎች በአብዛኛው ወይ በአንድ ክፍል ወገናዊነት ላይ
             የተመረኮዙ ምሉዕነት የጎደላቸው ይሆናሉ አለዚያም ሁሉንም ዝርዝር ጥያቄዎች በአንድ
             ጊዜ ለመመለስ በሚያደርጉት ጥረት መያዣ መጨበጫው የጠፋበት የመፍትሄ ሃሳብ ሆነው
             ይገኛሉ። በአንዳንድ ሁኔታም፣ መፍትሔ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የሚወሰዱ እርምጃዎች
             ችግሩን ይበልጥ ሲያወሳስቡት ይታያል።





                                                                        31
   34   35   36   37   38   39   40   41   42   43   44