Page 44 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 44

ደስታ መብራቱ


           3. መዋቅራዊ ችግሮቻችን ከምህዳራዊ እይታ አኳያ

                  ቀደም ባለው ክፍል፣ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ህመሞች ከምህዳራዊ አስተሳሰብ
           አኳያ የተመለከትን ሲሆን እነኚህን ህመሞች በአግባቡ ለመረዳት እና መፍትሄ ለመሻት
           ሊያግዙ የሚችሉትን መሰረታዊ የምህዳራዊ አስተሳሰብ መርሆዎችም ዳሠናል። በዚህም፣
           በፖለቲካችን  ውስጥ  ሊኖረን  የሚገባንን  ዋነኛ  የአመለካከት  ለውጥ  ለማምጣት
           የሚያስችሉንን መሰረት ለማስጨበጥ ተሞክሯል። በዚህ ክፍል ውስጥ ከፖለቲካችን ዋና
           ዋና መዋቅራዊ ችግሮች ጥቂቶቹን ቀደም ሲል ከቀረቡት የምህዳራዊ አስተሳሰብ መርሆዎች
           አኳያ ለመመልከት እንሞክራለን።

                                       14
           3.1 የፖለቲካችን መዋቅራዊ ችግሮች
                  የመጀመሪያው፣  በሃገራችን  ታሪክ ላይ  ያለው  ሁለት  ጽንፍ የያዘ  አመለካከት
           ነው። ባንደኛው ጽንፍ፣ ኢትዮጵያ ቀደምት እና እጅግ አኩሪ የሆነ ታሪክ ያላት አገር ናት
           በማለት  ባንዳንድ  የታሪክ  አጋጣሚ  የተፈጠሩ  አሳዛኝ  እና  አሳፋሪ  የታሪክ  ክስተቶች
           አልነበሩም፤  ቢኖሩም  በሌሎችም  ሃገሮች  ምስረታ  የታዩ  በመሆናቸው  የተለየ  ትኩረት
           አይገባቸውም ብሎ ያምናል። በሌላኛው ጫፍ ደግሞ፣ ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገር ከአንድ
           መቶ ሃያ ወይም ሰላሳ ዓመት ወዲህ በነበሩ ወረራዎች የተፈጠረች እና ታሪኳም የህዝቦች
           ጭቆና እና ግፍ ታሪክ ነው የሚል ነው። ስለሆነም ይህ ታሪክ ከመሰረቱ መቀየር አለበት
           ይላል።  በበርካታ  የሥነ  ህንጻ  እና  የቅሪተ  አካላት  ጥናቶች  እንደተረጋገጠው፣  ሃገራችን
           ኢትዮጵያ በአፍሪካም ሆነ በዓለም ልዩ ስፍራ የሚያሰጣት ቅድመ ታሪክም ሆነ ታሪክ
           እንዳላት ብዙም የሚያከራክር አይደለም። ያም ሆኖ ግን፣ እንደሌሎች ማንኛቸውም ሃገሮች
           ኢትዮጵያም  አሳፋሪ  የታሪክ  ምዕራፍ  አሳልፋለች።  በመሆኑም፣  ያለን  ብቸኛው  እና
           ጠቃሚው መንገድ የታሪካችንን መንትያ ገጽታዎች በመረዳት በአኩሪ እና ጠቃሚው ላይ
           መገንባት እና አሳፋሪው እና ጎጂው እንዳይደገም ለማድረግ መጣር ነው። እንዲህ ዓይነቱ
           አቀራረብ የምንፈልገውን የፖለቲካ ሥርዓት  በብሔራዊ መግባባት ላይ ለመገንባት ክፍተኛ
           አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
                  ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ በልጅነት አእምሮዬ ተቀርጾ የቀረን አንድ እውነተኛ ገጠመኝ
           ማካፈል  እፈልጋለሁ።  በአስራዎቹ  የመጀመሪያ  እድሜ  በነበርኩበት  ወቅት  ካወኳቸው
           ሰዎች  አንዷ ሲከፉ የምትባል  ሴት ነበረች። ይህች  ሴት በደቡባዊው የሃገራችን ክፍል
           ከሚገኝ እንድ ብሔረሰብ የመጣች ስትሆን፣ አብረን አንድ አካባቢ እስከኖርንበት ጊዜ ድረስ
           ውሎዋም ሆነ አዳርዋ በማዕድ ቤት ውስጥ ነበር። ይህች ሴት በወቅቱ ወደ አርባዎቹ
           የተጠጋ እድሜ የነበራት ስትሆን በተደጋጋሚ በእመቤት ተብዬዋ ስትደብደብ እና ስታለቅስ
           እያየሁ ሃዘን ይሰማኝ ነበር። መከፋቷ ሁሌም በፊቷ ላይ ይታይ ስለነበር፣ ሲከፉ የሚለው
           ስሟ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የወጣላት ይመስለኝ ነበር። አጋጣሚ ባገኘሁ ቁጥር ላጫውታት


           14  የዚህ ክፍል አብዛኛው፣ ሐምሌ 25 ቀን 2012 በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ የተነበበ ነው።
   39   40   41   42   43   44   45   46   47   48   49