Page 41 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 41
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
ሂደቶች (patterns) በአብዛኛው በግልጽ የሚታዩ እና ለስሜታዊ (emotive)
ምላሽ የሚያነሳሱ ናቸው።
iii. ያንድን የፖለቲካ ምህዳር መስረታዊ ህመሞች ለመረዳት እና መፍትሔ ለመሻት
ግን ሥልታዊ በሆነ መንገድ የሁነቶችን እና ሂደቶችን ጤናማነትንም ሆነ
ታማሚነት የሚወስኑትን መዋቅራዊ (structural) እና አእምሮአዊ ምንጮችን
(mental models) መመርመር ያሻል።
iv. ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሃገራችን ገነው የሚታዩ የፖለቲካ ውይይቶች እና
መጣጥፎች በአብዛኛው የሚያተኩሩት የተናጠል ሁነቶችን እና ሂደቶችን
በመተንተን እና በዚህም ላይ ተመርኩዘው ጥቅል የፖለቲካ አቋምን ማንጸባረቅ
ላይ ሆነው ይታያሉ። እንዲህ አይነቱ የፖለቲካ ነጥብ የማስቆጠሪያ አካሄድ
በብሔራዊ መግባባት ላይ የተመሰረተ እና የተረጋጋ ሃገራዊ የፖለቲካ ሥርዓት
ባለበት ሁኔታ ውስጥ ጠቃሚ እና የፖለቲካውም አካሄድ ዋነኛ መገለጫ ሊሆን
ይችላል። ዴሞክራሲያዊው ሥርዓት ባልደረጀበት ሁኔታ ግን ጽንፍ ለያዘ ንትርክ
ከማጋለጡ ባሻገር፣ ለተባባሰ የፖለቲካ ቀውስ ሊያጋልጥ ይችላል።
v. ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ህመሞች ዋነኛ ምንጭ ከሆኑት አእምሮአዊ ምንጮች
ቀዳሚዎቹ፤ ከሃገራዊው እውነታ ያልተጣጣሙ ጭፍን የአስተሳሰብ
እመርታዎች፣ ለረጂም ዘመናት በሃገሪቱ ተንሰራፍቶ የኖረው ባላባታዊ የፖለቲካ
ባህል፣ እና ውስብስብ ለሆነው የሃገሪቱ የፖለቲካ ችግር ቀላል የሆነ የፖለቲካ
መፍትሔዎች ለመሻት እና ለማራመድ የተደረጉ ጥረቶች ናቸው።
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ፣ ፖለቲካችንን ከመነሻው የተሳሳተ ቅርጽ ሲያስይዟቸው፣
የኋለኛው ችግሮች ይበልጥ አየተወሳሰቡ እንዲሄዱ አድርጓቸዋል።
vi. ከ1950ዎቹ ጀምሮ ከሃገራዊ እውነታ እና ተጨባጭ የህዝብ ፍላጎት ጋር
የማይጣጣሙ የፖለቲካ አስተሳሰቦች እና የማህበረሰብ እድገት ሞዴሎችን
በጅምላ እና በጭፍን ተቀብሎ ማህበራዊ መሰረቱን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ
ለማራመድ እና ለመተግበር መሞከር የፖለቲካችን ዋነኛው መለያ ሊሆን ችሏል።
እንዲህ ዓይነቱ አመለካከትም ከ1960ዎቹ ጀምሮ በሃገራችን ለተፈጠሩት
የፖለቲካ ምስቅልቅሎች ታላቁን ድርሻ እንዳበረከተ ይታመናል።
vii. የዘመናዊው ፖለቲካ አራማጅ ሆኖ የተነሳው የ1960ዎቹ (የእኔ) ትውልድ
በሃገሪቱ ከነበሩት የዘመናት ሃገራዊ የአስተዳደር እና የፖለቲካ ልምዶች
ጠቃሚውን ከመውሰድ ይልቅ በሚያሳዝን ሁኔታ የባላባታዊው ፖለቲካ ባህል
እስረኛ መሆኑ ሌላው አሳዛኝ ዕውነታ ነው። ይህም በመሆኑ፣ አብዛኞቹ አንጋፋ
የፖለቲካ ድርጅቶች በተሟላ ነፃነት ላይ ከተመረኮዘ ፖለቲካዊ አካሄድ ይልቅ
ፖለቲካዊ ጭሰኝነትን (political serfdom) የሚያራምድ የፖለቲካ አካሄድ
ሲተገብሩ ኖረዋል።
viii. ባላፉት ጥቂት ዓመታት የሚወጡ የፖለቲካ ትንተናዎች እና ጥናቶች ባብዛኛው
በተናጠል ሁነቶች እና ሂደቶች ላይ በሚያተኩር የተቀነበበ ትንተና ላይ
የተመረኮዙ በመሆናቸው የፖለቲካውን ግለት ከማፋፋም ያለፈ አስተዋጽኦ
33